loading
በነጻ ትምህርት ዕድል ሰበብ  ወደ ቻይና የሚጓዙ ዜጎች ችግር እየገጠማቸው ነው ተባለ

በነጻ ትምህርት ዕድል ሰበብ  ወደ ቻይና የሚጓዙ ዜጎች ችግር እየገጠማቸው ነው ተባለ። እስካሁን 47 ኢትዮጵያውያን ዜጎች ቻይና ውስጥ ታስረዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነቢያት ጌታቸው በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ ዜጎች ያለበቂ መረጃና ፈቃድ ወደ ቻይና በመሄድ ለከፍተኛ እንግልት እየተዳረጉ መሆኑን ተናግረዋል።

ለዚህም ዋናው ምክንያት በህገወጥ ደላሎች በኩል የሚነዛው የተሳሳተና የተጭበረበረ የነጻ የትምህርት ዕድል ቅስቀሳ ሲሆን በዚህም ዜጎች በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የህገወጥ አደንጻዥ ዕጽ በተለይም ጫት ዝውውር መረብ ሰለባ እየሆኑ ነው ብለዋል።

እንደ አቶ ነቢያት ገለጻ እስካሁን ከ47 በላይ ዜጎቻችን በቻይና ልዩ ልዩ ግዛቶች አደንዛዥ ዕጽ በማዘዋወር እና ጫት በማስመጣት፣ በግድያ ወንጀል፣ በስርቆት እና ሳይበር ክራይም፣ ያለ ቪዛ/መኖሪያ ፍቃድ ረዥም ጊዜ በመቆየት እና ያለስራ ፍቃድ በመስራት ወንጀሎች ታስረዋል።

 

የታሰሩ ሲሆን የተወሰኑት በተጠረጠሩት ወንጀል ተፈርዶባቸው የእርምት ጊዜያቸውን እየተከታተሉ እንዲሁም የተወሰኑት ደግሞ በተጠረጠሩበት ወንጀል በምርመራ ሂደት ላይ ናቸው ተብሏል።

ጫትን ጨምሮ አደንዛዥ ዕጽ በቻይና በህግ የተከለከለና የሞት ፍርድን ጨምሮ እስከ ዕድሜ ልክ እስራት የሚያስቀጣ በመሆኑ ከነጻ የትምህርት ዕድል ጋር በተያያዘ ለሚመጡ ያልተረጋገጡ መረጃዎች ህብረተሰቡ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርግ በመግለጫው  ተመልክቷል።

በጉዳዮ ዙሪያ መንግስት ቤጂንግ በሚገኘው ኤምባሲና በአራቱ ቆንስላ ጽ/ቤቶች በኩል ከቻይና መንግስት ጋር በመነጋገር ለችግሩ መፍትሄ ለማበጀት እየሰራ መሆኑንም አቶ ነቢያት ጠቁመዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *