loading
በአውሮፕላን አደጋ ሕይወታቸውን ላጡት ኢትዮጵያዊያን የመታሰቢያ ሐውልት ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 19፣ 2013 በአውሮፕላን አደጋ ሕይወታቸውን ላጡት ኢትዮጵያዊያን የመታሰቢያ ሐውልት ::ከሁለት ዓመታት በፊት በተከሰተው የአውሮፕላን አደጋ ሕይወታቸውን ላጡት ኢትዮጵያዊያን የመታሰቢያ ሐውልት ሊቆምላቸው ነው ::ከሁለት ዓመታት በፊት በተከሰተው የአውሮፕላን አደጋ ሕይወታቸውን ላጡት ኢትዮጵያዊያን የመታሰቢያ ሐውልት ሊቆምላቸው ነው። አደጋው የደረሰበት የግምቢቹ ወረዳ ቱሉፈራና አጎራባች ቀበሌዎች ነዋሪዎች ተጠቃሚ የሚያደርጉ አራት ፕሮጀክቶችም ሊተገበሩ መሆኑ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ጽ/ ቤት ዋና ጸሐፊ ዶክተር አባ ተሾመ ፍቅሬ እንዳሉት ቦይንግ ኩባንያ ለተጎጂ ቤተሰቦች በሰጠው ድጋፍ መሰረት በኢትዮጵያ  ጉዳት የደረሰባቸው 18 ሰዎች ቤተሰቦች አደጋው በደረሰበት ስፍራ ያሉ ነዋሪዎች ላደረጉት ሰብዊነት በስፍራው ሐውልት እንዲሰራ ይሁንታ ሰጥተዋል።

የሰውነት ተምሳሌት የሆናችሁ ነዋሪዎች ከአሳዛኙ አደጋ ለተጎዱ ዜጎች ያደረጉት ክብር አድንቀው፤ አደጋ በደረሰበት ስፍራ ነዋሪዎች በአደጋው ያለፉ ሰዎች ሰው በመሆናቸው ብቻ ተጎጂዎች ያደረጉት ተግባር ከቦይንግ በተገኘ ገንዘብ ድጋፍ አምስት አይነት ፕሮጀክቶች እንዲተገበሩም ተወስኗል። ፕሮጀክቶቹ ባለፉት የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የልማት ድርጅት አማካኝት የሚተገበር ሲሆን የፕሮጀክቶችን ክ ንውን የሚቆጣጠር ከኦሮሚያ ክልልና ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የተውጣጣ ኮሚቴ መዋቀሩን ተናግረዋል።

ይህ ተግባር በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ፈፃሚነት ስራዎች መጀመራቸውንና ገልጸው ፤ፕሮጀክቶችም ሶስት ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶች፣ እያንዳንዳቸው 5 ብሎክ ህንፃዎች ያላቸው ሁለት የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ይሰራሉ።አንድ ጤና ኬላ ግንባታና  ሰባት ድልድዮችም የፕሮጀክቱ አካል ናቸው ተብሏል።ከዚህ በተጨማሪ ጉዳት የደረሰበቫቸው 18 ኢትዮጵያዊያን የመታሰቢያ ሐውልት አደጋው በደረሰበት ስፍራ እንዲቆምላቸው ይደረጋል ነው ያሉት።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *