loading
ትራምፕ ኮሮረናቫይረስ አሜሪካዉያንን እንደጎዳ አመኑ::

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 5፣ 2012 ትራምፕ ኮሮረናቫይረስ አሜሪካዉያንን እንደጎዳ አመኑ::ሲ ኤን ኤን እንደዘገበዉ ትራምፕ ኮሮና ቫይረስ በአሜሪካ እነደተገኘ በመጀመሪያዎቹ ሳመንታት ቫይረሱ አደገኛ እንደሆነ ያዉቁ እንደነበር ተናግረዋል ብሏል፡፡ትራምፕ ከታዋቂዉ ጋዜጠኛ ቦብ ዉድዋር ጋር ባደረጉት የድምጽ ቅጂ ቃለ ምልልስ ፤ ኮሮና ቫይረስ በጣም አደገኛ በትንፋሽ የሚተላለፍ ፤በፍጥነት የሚዛመት ከዚህ በፊት ከነበሩ ጎንፋኖች በጣም ገዳይ መሆኑን ያዉቁ እንደነበር ተናግረዋል ተብሏል፡፡

አሁንም ቢሆን ስለቫይረሱ በማጋነን ሽብር መፍጠር አልፈልግም ብለዋል ፕሬዚዳንቱ ፡፡በርካታ አሜሪካዉያን ኮሮና ቫይረስ በሀገሪቱ እንደተከሰ መወሰድ የነበረባቸዉ ቫይረሱን የመከላከል እርምጃዉች በግዜዉ ቢወሰዱ ኖሮ ጉዳት ሳይድርስ የብዙ አሜሪካዉያንን ህይወት መታደግ ይቻል ነበር ብለዉ እንደሚያምኑ ዘገባዉ ጠቅሷል፡፡ይሁንና ትራምፕ ቫይረሱን የቻይና ጉንፋን ከማለት የዘለለ ክብደት ባለመስጠታቸዉ አሜሪካ በቫይረሱ በተያዙ ሰዎችም በሟቹችም ቀቁጥር አለምን እየመራች ነዉ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *