ነገ ለሰባት ሚሊዮን ሰዎች አገልግሎት የሚሰጥ ሆስፒታል ይመረቃል
ነገ ለሰባት ሚሊዮን ሰዎች አገልግሎት የሚሰጥ ሆስፒታል ይመረቃል
አርትስ 30/02/2011
ነገ የሁለት አገር መሪዎችን በምታስተናግደው ባህርዳር ከተማ የሚመረቀው ሆስፒታል ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በሚል ተሰይሟል፡፡ 207,221,970.00 ብር ወጪ የተደረገበት ሲሆን ሙሉ በሙሉ አገልግሎት ሲጀምር 2000 ህሙማንን በቀን የማስተናገድ አቅም አለው :: ከዚህም በተጨማሪ ከ5-7 ሚሊዮን ያህል ዜጎችን በቀጥታ ተጠቃሚ ማድረግ ይችላል:: ሆስፒታሉ 500 አልጋዎች የሚኖሩት ሲሆን እስከአሁን ድረስ 11 የኦፐሬሽን ክፍሎች አሉት :: የኦፕሬሽን ክፍሎቹን ቁጥር ወደ 15 ያሳድጋል:: ሆስፒታሉ በርከት ያሉ ተጨማሪ ክፍሎች እንደሚኖሩት አርትስ ያገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ በዚህም ለባህር ዳር እና አካባቢው ነዋሪዎች አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ሶስተኛው ሆስፒታል ይሆናል:: ይህም በመሆኑ በፈለገ ህይወት ሆስፒታል ላይ ያለው ጫና በማቃለል የአገልግሎት ጥራቱን ለማሻሻል ጉልህ አስተዋፅኦ ያበርክታል ተብሏል::