loading
አራት ኢትዮጵያዊያን ሴቶች ከ100 የአፍሪካ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶች ስም ዝርዝር ዉስጥ ተካተቱ::

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 27፣2013 አራት ኢትዮጵያዊያን ሴቶች ከ100 የአፍሪካ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶች ስም ዝርዝር ዉስጥ ተካተቱ::አራት ኢትዮጵያዊያን ሴቶች ከ100 የአፍሪካ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶች ስም ዝርዝር ዉስጥ መካተታቸው ተገለፀ፡፡ በየዓመቱ 100 የአፍሪካ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶችን ስም ዝርዝር የሚያወጣው አቫንስ ሚዲያ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ 4 ኢትዮጵያዊያን በስኬታማና ተፅዕኖ ፈጣሪ 100 አፍሪካዊያን ሴቶች መዝገብ ውስጥ አካቷቸዋል።
ከፕሬዚዳንቷ በተጨማሪ ከመቶ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሴቶች ውስጥ የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስትር ፊልሰን አብዱላሂ፣ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ እና የሶል ሪቤልስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ቤተልሄም ጥላሁን ተካተውበታል፡፡

የተመረጡት በየዓመቱ ስኬታማና ውጤታማ የሆኑ 100 የአፍሪካ ሴቶችን ስም ዝርዝር ያወጣው አቫንስ ሚዲያ የአመራርና አፈፃፀም ክህሎት፣ በግል  ያስመዘገቡት ስኬት፣ እውቀት የማጋራት ቁርጠኝነት እንዲሁም የተለመዱና ምቹ ያልሆኑ አሰራሮችን የመቀየር አቅም የሚሉት መስፈርቶች የመምረጫ ነጥቦች መሆናቸውን ድርጅቱ በድረገጹ አስታውቋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *