loading
አጣየን መልሶ ለመገንባት የተጀመረ ጥረት

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26 ፣ 2013  የወጣት ማህበራት የአጣዬ ከተማና አካባቢው ተጎጂዎችን እንዲቋቋሙ ለማገዝ ሃብት ማሰባሰብ ጀመሩ በአማራ ክልል አጣዬ ከተማንና አካባቢው ተጎጂዎችን መልሶ ለማቋቋም መንግስት የሚያደርገውን ጥረት ለማገዝ ሃብት የማሰባሰብ ሰራ መጀመሩን በክልሉ የወጣት ማህበራት አመራሮች አስታውቀዋል፡፡ የክልሉ ወጣቶች ማህበር ዋና ፀሐፊ ወጣት ከፍያለው ማለፎ ለኢዜአ እንደገለጸው፤ በአጣዬ ከተማ በደረሰው ጉዳት የክልሉን ወጣቶችን አሳዝኗል።

የከተማውንና አካባቢውን ተጎጂዎች መልሶ ለማቋቋም የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ አደረጃጀት ተፈጥሮ የመቀስቀስና የጉዳት መጠኑን የመለየት ስራ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ እየተከናወነ መሆኑንም ተናግሯል። ሃብት የማሰባሰብ ስራውን እስከ ግንቦት 10/2013 ዓ.ም. ለማጠናቀቅ ታስቦ ወደ ስራ መገባቱን
ጠቅሶ፤ መንግስት የአጣዬ ከተማን ለመገንባት ከሚያደርገው እንቅስቃሴ በተጨማሪ ወጣቱ የራሱን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ሀብት የማሰባሰብ ስራ መጀመሩን አስታውቋል።

ሃብት የማሰባሰብ ስራው ቤታቸው የተቃጠለባቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ቤት ለመገንባት የሚያስችል ቆርቆሮና ሌሎች የፋብሪካ ውጤቶች ግዥን የሚያጠቃልል መሆኑን ወጣት ከፍያለው ጠቅሷል። በተጨማሪም ሃብት ንብረታቸው የወደመባቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች እለታዊ ችግራቸውን ለማቃለል
የሚያግዙ አልባሳትና ምግብ እህል የመሰብሰብ ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተነግሯል። ስራውን በተደራጀ አግባብ ለመምራት ከሁሉም ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ የወጣት ተወካዮች አስፈላጊው ግንዛቤ ተፈጥሮላቸው ወደ ስራ መግባታቸውም ተገልጿል፡፡ማህበረሰቡም ወጣቱ የጀመረውን የአጣዬ ከተማንና አካባቢዋን ማህበረሰብ መልሶ ለማቋቋም ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ወጣቶቹ መልዕክት አስተላልፈዋልል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *