loading
እስራኤል እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች አዳዲስ ስምምነቶችን ተፈራረሙ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2013  እስራኤል እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች አዳዲስ ስምምነቶችን ተፈራረሙ::በቅርቡ የዲፕሎማሲ ስምምነት ያደረጉት ሁለቱ ሀገራት ያለ ቪዛ ጉዞዎችን መፍቀድን ጨምሮ አራት የሚሆኑ ስምምነቶችን ተፈራርመዋል ነው የተባለው፡፡ሌሌቹ የስምምነት ዘርፎች ደግሞ የአቬሽን ኢንዱስትሪ፣ የኢኮኖሚ ትብብር እና ኢንቨስትመንትን የተመለከቱ ናቸው፡፡

አልጀዚራ እደዘገበው ቴል አቪቭ እና አቡዳቢ በቅርቡ የጀመሩት የዲፕሎማሲ ግንኙነት በፍጥነት መሻሻል እየታየበት ነው፡፡ሁለቱ ሀገራት በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አደራዳሪነት ያደረጉት ስምምነት እስራኤል ከአረብ ሀገራት ጋር ለሚኖራት ግንኙነት ፈር ቀዳጅ ነው ተብሎለታል፡፡

ይሁን እንጂ ስምምነቱ ፍልስጤምን የሚጎዳ ነው ብለው የሚያስቡ አንዳንድ ሀገራት የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶችን አጥብቀው ከመውቀስ አልተቆጠቡም፡፡ፍልስጤማዊያን አቡዳቢ ከእስራኤል ጋር በመስማማቷ ክህደት ፈፅማብናለች በማለት ሲከሱ ኢራን በበኩሏ እስራኤል በገልፍ ሀገራት ለምታደርሰው ጥፋት ተጠያቂ ከመሆን አትድንም ብላታለች፡፡አሜሪካ ሌሎች የአረብ ሀገራትም የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶችንና የባህሬንን ፈለግ ተከትለው ከእስራኤል ጋር የዲፕማሲ ግንኙነት እንዲያደርጉ እያግባባች ትገኛለች፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *