loading
ከንቲባ ታከለ ኡማ በዛሬው እለት ከግብር ከፋይ ነጋዴዎች ጋር ይወያያሉ ተባለ

ከንቲባ ታከለ ኡማ በዛሬው እለት ከግብር ከፋይ ነጋዴዎች ጋር ይወያያሉ ተባለ

አርትስ 11/04/2011

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ፅ/ቤት፣ ከከተማው ገቢዎች ባለስልጣን ጋር በመተባበር ዛሬ 2000 ከሚሆኑ የመርካቶ እና አካባቢው ግብር ከፋይ ነጋዴዎች ጋር ውይይት ሲያደርግ

የውይይቱ ዋነኛ አላማ ለንግዱ ማህበረሰብ ምቹ የንግድ አካባቢ በሚፈጠርበት እና ፍትሃዊ የመወዳደሪያ ሜዳ በሚመቻችበት ሁኔታ ላይ እና የንግዱን ማህበረሰቡን ችግር በመቅረፍ፤ ግብር ከፋዩ የለውጡ አካል በሚሆንበት ሁኔታ ላይ ለመመካከር መሆኑን ከከንቲባ ፅ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

የውይይት መድረኩን ከንቲባ ታከለ ኡማ የሚመሩት ሲሆን  በገቢዎች ባለስልጣን የተዘጋጀ አጭር የመነሻ ሃሳብ ከቀረበ በኃላ ከንቲባው ከግብር ከፋይ ነጋዴዎች ጋር ውይይቱን ያደርጋሉ ተብሏል፡፡

 

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *