ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ የምርጫ ድምፅ ቆጠራውን በድጋሜ እንድታካሂድ ተጠየቀች
ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ የምርጫ ድምፅ ቆጠራውን በድጋሜ እንድታካሂድ ተጠየቀች
ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ያካሄደችው ፕሬዚዳንታዊ የምርጫ ፉክክር የድምፅ ቆጠራ ውጤት ይፋ ቢደረግም፤ በተፎካካሪዎች ዘንድ የተሳሳተ ነው መባሉን ተከትሎ የደቡብ አፍሪካ ልማት ማህበረሰብ (ሳድክ) የድምፅ ቆጠራውን በድጋሜ እንድታከናውን ጥሪ አቅርቦላታል፡፡
ኮንጎ ነፃነቷን ከተቀዳጀች ከ59 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ዴሞክራሲያዊ የስልጣን ሽግግር ማብሰሪያ ይሆናል ብሎ ተስፋ የተጣበት ምርጫ ከሁለት ሳምንት በፊት ተካሂዶ ነበር፡፡
የተቃዋሚው ፓርቲ መሪ ፊሊክስ ሸሲኪዲ እና ካቢላ ጥምረት ፈጥረው አሸናፊነታቸውን ሊያውጁ ነው ቢባልም የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ሽስኬዲ በጠባብ የድምፅ ብልጫ ማርቲን ፋዩሉን አስከትለው አሸንፈዋል ሲል ይፋ አድርጓል፡፡
በምርጫው ተፎካካሪ የነበሩት እና በተሰጠው ድምፅ ሁለተኛ የወጡት ፋዩሉ ግን አሸናፊነት ይገባኛል እያሉ ነው፡፡
ሽስኬዲ እና ካቢላም ስለ ተባለው ጥምረት አስቀድመው አሉባልታ ነው ብለዋል፡፡
የኮንጎ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ደግሞ በምርጫው ያሰማራኋቸው 40 ሺ ጠንካራ ታዛቢዎቼ ያደረሱኝ የድምፅ ውጤት አሸናፊ ኮሚሽኑ ይፋ ካደረገው የተለየ ነው ብላለች፡፡
ሳድክ ባወጣው መግለጫም በአሸናፊዎቹም ሆነ ተሸናፊዎች ወገን መተማመን ለመፍጠር ሲባል የድምፅ ቆጠራው በድጋሜ ቢደረግ የሚል ነው፡፡
ሳድክ የካቢላ አጋር አንጎላን እና ደቡብ አፍሪካን የመሳሰሉ ሀገራትን ያቀፈ ሲሆን የካቢላ፣ ፋዩሉ እና ሽሲኬዲ የሚወክሏቸው ፓርቲዎች ለሀገሪቱ ብሔራዊ ህብረት ሲባል ሰላምን እንዲዘምሩ አሳስቧል፡፡
ይሁን እንጂ ይህ አይነቱ ህብረት በኮንጎ የሚታይ አይመስልም፡፡ ምክንያቱም የካቢላ ቀንደኛ ተቀናቃኝ ፋዩሉ ይፋዊ ቅሬታቸውን በሳምንቱ መጨረሻ ለሀገሪቱ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት አስገብተዋል ሲል አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል፡፡