loading
የቀድሞው የማሊ ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ቡበከር ኬታ ለህክምና ወደ አቡዳቢ መጓዛቸው ተሰማ::

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 2፣ 2012 የቀድሞው የማሊ ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ቡበከር ኬታ ለህክምና ወደ አቡዳቢ መጓዛቸው ተሰማ:: በቅርቡ በወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ከስልጣን የተባረሩት ኬታ ህክምናቸውን ለመከታተል ወደ ተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች መጓዛቸውን የቀድሞው የጦር አዛዣቸው ማማዱ ካማራ ተናግረዋል፡፡
ለአስር ቀናት ያህል በወታራዊ ጁንታው ቁጥጥር ስር የነበሩት ኬታ ባማኮ ውስጥ በሚገኝ አንድ የግል የህክምና ተቋም የጤናቸውን ሁኔታ ሲከታተሉ ነበር፡፡
የኬታ ህመም በትክክል ባይገለፅም ከስትሮክ ጋር ተቀራራቢነት ያለው እንደሆነ ውስጥ ውስጡን ይነገራል፡፡

መፈንቅለ መንግስተ አድራጊዎቹ ገና በቁጥጥራቸው ስር ሳሉ ለምእራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ኢኩዋስ በገቡት ቃል መሰረት ነው ከእስር ከለቀቋቸው በኋላ ውጭ ሀገር እንዲታከሙ የፈቀዱላቸው፡፡ ፕሬዚዳንቱ ወደ አቡዳቢ ሲሄዱ ባለቤታቸውና የደህንነት ሰዎች አብረዋቸው እንደተጓዙ ሮይተርስ
የዲፕሎማሲ ምንጮች ንጠቅሶ ዘግቧል፡፡ በማሊ የሲቪል መንግስት ይመስረት በሚለው ጉዳይ ላይ ድርድሩ እንደቀጠለ መሆኑን ዘገባው አክሎ
ገልጿል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *