የአፍሪካ ህብረት ለአህጉሪቱ ሳይንስ ቴክኖሎጂና ፈጠራ ልማት ጥሪ አቀረበ
የአፍሪካ ህብረት ለአህጉሪቱ ሳይንስ ቴክኖሎጂና ፈጠራ ልማት ጥሪ አቀረበ
አርትስ 26/02/2011
የህብረቱ የሰው ሀብት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሊቀመንበር አያንግ አግቦር የመጀመሪያው በትምህርት ሳይንስ ቴክኖሎጂ እና ፈጠራ ላይ ያተኮረው ስብሰባ ትናንት ሲካሄድ እንዳሉት ለአፍሪካ 2063 ዕቅድ ስኬት አገራት ዘርፎቹን በፖሊሲና ስትራቴጂ ሊደግፉ ይገባል፡፡
ስብሰባው የ10 አገራት ልዩ ኮሚቴዎችን አካቶ በማላዊ ሊሎንጉዌ ከተማ የተካሄደ ሲሆን በቀጣይ በሚካሄደው የህብረቱ ጉባዔ ሀሳብ ለማቅረብ እንደሚያግዝ ተነግሯል፡፡