![](http://43.156.135.34.bc.googleusercontent.com/wp-content/uploads/2018/10/43753680_2638320203058858_3975190462368579584_n.jpg)
የጠቅላይ ሚኒስትር የአውሮፓ ጉብኝትን በተመለከተ በፍራንክፈርት ቆንስላ የውይይት መድረክ ተዘጋጀ::
አርትስ 02/02/2011
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ እ.ኤ.አ. ኦክቶበር 31 ቀን 2018 ዓ.ም በአውሮፓ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በፍራንክፈርት ይወያያሉ።
ጉብኝቱን በተመለከተ በፍራንክፈርት ቆንስላ የውይይት መድረክ ተዘጋጅቷል።
የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃላ አቀባይ ጽ/ቤት እንዳስታወቀዉ በአውሮፓ የሚገኙ ኤምባሲዎችም ሁኔታዎችን በማመቻቸት የተቀናጀ ሥራ ለመሥራት ዕቅድ አውጥተው በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸዉን ገልጸዋል፡፡