loading
ዲዲዬር ድሮግባ የዓለም ጤና ድርጅት የስፖርት እና የጤና አምባሳደር ሆኖ ተሾመ፡፡

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 09፣ 2014  የቀድሞው ኮትዲቯሪያዊው እግር ኳስ ተጫዋች በጤና ድርጅቱ የአምባሳደርነት ሚና ሲሰጠው በአካላዊ እንቅስቃሴዎች አስፈላጊነት ላይ የድርጅቱን መመሪያ የማስተዋወቅ ኃላፊነት ተጥሎበታል ተብሏል፡፡ ድሮግባ የዓለም ጤና ድርጅት የመልካም ፍቃድ የስፖርት እና ጤና አምባሳደር ስብስብ በመቀላቀሉ ደስታ እንደተሰማው የተናገረ ሲሆን የ2022 የዓለም ዋንጫን ጤናማ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ለማድረግ በዓለም ጤና ድርጅት፣ በፊፋ የዓለም ዋንጫ እና በኳታር መካከል ያለው የቡድን ሥራ ጠንካራ መሆኑን ተናግሯል። የዚህ አካል በመሆኑም የተሰማውን ኩራት አንፀባርቋል።

የቀድሞው ተጫዋች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ጥቅሞችን እና ሌሎች ጤናማ የአኗኗር ዘይቤዎችን በተመለከተ የድርጅቱን መመሪያ ለማስተዋወቅ ድርጅቱን ያግዛል የተባለ ሲሆን ሰዎች በተቻለ መጠን ከፍተኛ የጤና ደረጃ ላይ እንዲደርሱ ለማገዝ መሰናዳቱንና በተለይም በሁሉም ሃገራት ያሉ ወጣቶች ላይ
ያለውን ጤናማነት ለማሻሻል እንደሚሰራ ቃሉን ሰጥቷል። የሁለት ጊዜ የአፍሪካ የዓመቱ ኮከብ ተጫዋች አሸናፊው እንዲህ ዓይነቱን መልካም ተግባር በዓለም
ዙሪያ ለማካፈል ከዓለም ጤና ድርጅት ጋር ለመስራት ያለውን ቁርጠኝነት ገልጿል፡፡

ድሮግባ በድርጅቱ ውስጥ ሚናውን ማግኘታቸው መታደላቸውን የሚናገሩት ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በዓለም ዙሪያ ያሉ ማህበረሰቦች ለአካላዊ እና ለአእምሮ ጤንነታቸው እንዲሁም ለደህንነታቸው በስፖርት ታግዘው ግባቸው ላይ እንዲደርሱ በሚያደርገው እገዛ ደስተኞች ነን ብለዋል። ከድሮግባ በተጨማሪ ብራዚላዊው ኮከብ አሊሰን ቤከር፣ ማይክል ብሉምበርግ፣ ሲንቲያ ጌርማኖታ እና የቀድሞው የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ጎርደን ብራውን የዓለም ጤና ድርጅት አምባሳደር ከሆኑት መካከል ይገኙበታል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *