loading
ግብፅ ከሩሲያ ዘመናዊ የጦር አውሮፕላኖችን ልትገዛ ነው፡፡

ግብፅ ከሩሲያ ዘመናዊ የጦር አውሮፕላኖችን ልትገዛ ነው፡፡

ግብፅ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2020 እና 2021 የሚጠናቀቅ የ20 ተዋጊ ጀቶች የግዥ  ስምምነት ከሩሲያ ጋር  ተፈራርማለች፡፡

በሩሲያ የሚታተመው እለታዊ ጋዜጣ ኮሜርሳንት እንደዘገበው ግብፅ የምትገዛቸው የጦር ጀቶች ኤስ ዩ 35 የተሰኙ እና በአንድ ጊዜ እስከ 24 ዒላማዎችን የመለየት ብቃት አላቸው፡፡

አራተኛው ትውልድ በመባል የሚታወቁት እነዚህ ተዋጊ አውሮፕላኖች በሩሲያ ጦር ሀይል ለመጀመሪያ ጊዜ ስራ ላያ የዋሉት በፈረንጆቹ 2014 ነው፡፡

ግብፅ ኤስ ዩ 35 የተሰኙትን ተዋጊ ጀቶች ከሩሲያ ለመግዛት ቻይናና ኢንዶኔዥያ ብቻ ናቸው የቀደሟት ተብሏል፡፡

ካይሮ አነዚህን የውጊያ አውሮፕላኖች ለመሸመት ከ2 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ታወጣለች ነው የተባለው፡፡

ግብፅ በአሁኑ ጊዜ ከሩሲያ ከፍተኛ  የጦር መሳሪያ ግዥዎችን ከሚፈፅሙ ሀገራት ተርታ እንደምትመደብ በዘገባው ተጠቅሷል፡፡

 

መንገሻ ዓለሙ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *