loading
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድና   የሶማሊላንድ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ የሁለቱ ሀገራትን ግንኙት በተመለከተ ተወያዩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድና   የሶማሊላንድ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ የሁለቱ ሀገራትን ግንኙት በተመለከተ ተወያዩ።

ሁለቱ ወገኖች በሀገራቱ መካከል ያለውን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ይበልጥ ስለማጠናከር፣ በሶማሊላንድ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ደህንነት ስለማስጠበቅና በሰላም ዙሪያ ተባብሮ ስለመሥራት ተወያይተው ስምምነቶች ላይ ደርሰዋል።

ፕሬዝዳንት ሙሴ ዶክተር አብይ ለቀጣናው ውህደት የወሰዷቸውን ርምጃዎች በማስታወስ  አስተዳደራቸው ከሶማሊያ መንግሥት ጋር በይብልጥ ተቀራርቦ አብረው እንዲሠሩ  ዶክተር አብይ ያቀረቡትን ጥሪ እንደሚቀበሉ ገልጸዋል።

በተጨማሪም ወደፊት በጋራና በተናጠል ቀጣይ ውይይቶችን ለማካሄድ ተስማምተዋል።  ሁለቱ ወገኖች ስለ ወደብ አጠቃቀምና ሌሎችም የኢኮኖሚ ትሥሥር ላይ መወያየታቸዉን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *