loading
ፓሪስ በተቃውሞ ሰልፍ እየተናጠች ለአራተኛ ሳምንት ዘልቃለች

ፓሪስ በተቃውሞ ሰልፍ እየተናጠች ለአራተኛ ሳምንት ዘልቃለች

አርትስ 30/03/2011

የፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን መንግስት በነዳጅ ላይ ተጨማሪ ቀረጥ ሊጥል መሆኑ ከተሰማ ወዲህ ፓሪስና አካባቢዋ የሰላም አየር መተንፈስ አቅቷቸዋል፡፡

የፈረንሳይ መንግስት በፓሪስ ከተማ ብቻ 8 ሺህ የፖሊስ አባላትን አሰማርቶ አመፁን ለማስቆም ያደረገው ጥረት ብዙም ውጤታማ አልሆነም፡፡

ሲ ኤን ኤ እንደዘገበው በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት ብቻ ፓሪስ ውስጥ ሰልፈኞቹ ከፖሊሶች ጋር ባደረጉት ግጭት 135 ሰዎች ቆስለዋል፡፡

ሩሲያ ቱዴይ በዘገባው እንዳሰራጨው በመላው ፈረንሳይ ከ90 ሺህ ባለይ ሰዎች ለተቃውሞ ሰልፍ ጎዳና ወጥተዋል፡፡

የፈረንሳይ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ያፓሪስ ከተማን መተንፈሻ ያሳጧት 10 ሺህ የተቃውሞ ሰልፈኞች አሁንም ከፖሊስ ጋር ግብግብ ላይ ናቸው፡፡

ፖሊስ እስካሁን 1ሺህ 723 ሰወችን ለጥያቄ ጣቢያ የወሰደ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 1 ሺህ 220 የሚሆኑትን በእስር እንዲቆዩ አድርጓል፡፡

አመፁን ተከትሎ ለወትሮው የክሪስማስ ገበያ ከምንጊዜውም በላይ በሚሟሟቅባት የፓሪስ ከተማ ሁሉም ሱቆች በራቸውን አጥብቀው ዘግተው መጭውን ጊዜ በትግእስት እየተጠባበቁ ነው፡፡

አመፁ ተባብሶ እንዳይቀጥል ስጋት ያደረበት የፈረንሳይ መንግስት  89 ሺህ የፀጥታ ሰራተኞችን በመላ ሀገሪቱ በማሰማራት ላይ እንደሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኤድዋርድ ፊሊፕ ተናግረዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *