loading
የአዲስ አበባ ከተማ ከተማ አስተዳደር ለመከላከያ ሰራዊት ለሁለተኛ ጊዜ ያሰባሰበውን 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ የገንዘብና የዓይነት ድጋፍ አስረከበ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2013 የአዲስ አበባ ከተማ ከተማ አስተዳደር ለመከላከያ ሰራዊት ለሁለተኛ ጊዜ ያሰባሰበውን 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ የገንዘብና የዓይነት ድጋፍ አስረከበ ከድጋፉ 1 ነጥብ 1 ቢሊዮን የሚሆነው በጥሬ ገንዘብ ሲሆን እና 180 ሚሊዮን ብር የሚያወጣው ደግሞ በዓይነት ነው፡፡ የከተማ አስተዳደሩን ድጋፍ የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቀነዓ ያደታ ተረክበዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ጳጉሜ 4 የጀግንነት ቀን ክብር በዓል እንዲሆን የተወሰነው ኢትዮጵያ ያሏትን ጀግኖችን ለማውሳት
መሆኑንም በስነ ስርዓቱ ላይ አመልክተዋል፡፡

የኢትዮጵያ የጀግንነት ታሪክ በደምና በአጥንት የተፃፈባት መሆኗን አለም ያውቀዋል ያሉት ምክትል ክንቲባዋ ፣ኢትዮጵያዊነትና ጀግንነት የማይነጣጠሉ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ ከዘመን ዘመን ከትውልድ ትውልድ ስሟን የሚያስጠሩ ጀግኖችን አጥታ አታውቅም ያሉት ወ/ሮ አዳነች፤ በአሁን ሰዓት ለኢትዮጵያ ሰላምና አንድነት መጠበቅ ህይወታቸውን እየሰጡ የሚገኙ ጀግኖች
የላቀ ክብርና ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል፡፡ በዚህ ወቅት ሁሉም ሰው ለሀገሩ አርበኛ ነው፤ ኢትዮጵያ ጀግኖች እያሉ አትሸነፍም አትፈርስም
፤ከሁሉም በላይ ህይወታቸውን ለሀገራቸው መስዋዕት እያደረጉ ያሉ የፀጥታ ኃይሎች ገድል ከጀግንነት ሁሉ በላይ ጀግንነት ነው ብለዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ለጀግኖች በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ቅድሚያ እንዲሰጣቸው ወስኖ
ተግባራዊ እያደረገ እንደሚገኝም አስታውቀዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *