loading
ኢትዮጵያዊያን አምባሳደሮች አመታዊ  ጉባኤያቸውን እያካሄዱ ነው ፡፡

ኢትዮጵያዊያን አምባሳደሮች አመታዊ  ጉባኤያቸውን እያካሄዱ ነው ፡፡ ኢትዮጵያን በውጭ የሚወክሉ አምባሳደሮች ቆንስላ ጄኔራሎች እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዳይሬክተር ጄኔራሎች የሚሳተፉበት ጉባኤ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ነው፡፡ ጉባኤው  በዋናነት የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት  እና በውጭ የሚገኙ ሚሲዮኖች የስራ እንቅስቃሴ ፣የሚያጋጥሙ  ችግሮች እና መፍትሄዎቸቻው ላይ ያተኩራል ተብሏል፡፡ ሌላው የውይይቱ አጀንዳ ክልላዊ እና ዓለምአቀፋዊ ጉዳዮች በኢትዮጵያ እና በጎረቤት አገራት […]

በአማራና ትግራይ ህዝቦች መካከል ግጭትም የግጭት ፍላጎትም የለም አሉ የሁለቱ ክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮች

በአማራና ትግራይ ህዝቦች መካከል ግጭትም የግጭት ፍላጎትም እንደሌለ የሁለቱ ክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮች ገለጹ። የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች በተለያዩ አካባቢዎች ሲያደርጉት የነበረውን የሰላም ጉዞ አስመልክቶ በአዲስ አበባ የማጠቃለያ መድረክ አካሄደዋል። በመድረኩ ላይም ከተለያዩ የሀይማኖት ተቋማት የተውጣጡ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የክልል ርእሳነ መስተዳድሮች ተሳትፈዋል። በመድረኩ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው እና […]