loading
ኤርባስ ኤ 380 የተሰኘውን አውሮፕላን ማምረት አላዋጣኝም አለ፡፡

ኤርባስ ኤ 380 የተሰኘውን አውሮፕላን ማምረት አላዋጣኝም አለ፡፡ በአውሮፓ ትልቁ አውሮፕላን አምራች ኤር ባስ ኩባንያ በፈረንጆቹ 2021 ሱፐር ጃምቦ ጀት የመንገደኞች አውሮፕላን ማምረቱን ለማቆም ማሰቡን ይፋ አድርጓል፡፡ ኤር ባስ ምርቱን ለማቆም የተገደድኩት ገበያው ስለተቀዛቀዘ ነው ማለቱን አልጀዚራ በዘገባው አስነብቧል፡፡ ኤር ባስ ይህን አውሮፕላን ማምረት የጀመረው ከቦይንግ 747 ጋር በመፎካከር የገበያ ድርሻውን ለመቆጣጠር ቢሆንም አብዛኞቹ አየር […]

ሪያድ ወደ ውጭ የምትልከውን የነዳጅ መጠን ልትቀንስ ነው፡፡

ሪያድ ወደ ውጭ የምትልከውን የነዳጅ መጠን ልትቀንስ ነው፡፡ ሳውዲ አረቢያ ከመጭው መጋቢት ወር ጀምሮ በቀን ወደ ውጭ ትልከው የነበረውን 8.2 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ ወደ 6.9 ሚሊዮን በርሜል ዝቅ ልታደርግ መሆኑን ተናግራለች፡፡ የሳውዲ የኢነርጂ ሚኒስትር ካሊድ አል ፋሊህ ለፋይናንሺያል ታይምስ እንደተናገሩት ሪያድ ወደ ውጭ የምትልከውን ነዳጅ ብቻ ሳይሆን የምርት መጠኗንም የመቀነስ ሃሳብ አላት፡፡ በዓለም አቀፉ የነዳጂ […]

የኢሳት ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች ወደ ኢትዮጵያ ገቡ

የኢሳት ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች ወደ ኢትዮጵያ ገቡ ለ20 ዓመታት ከሃገር ውጭ የነበሩ የኢሳት ቴሌዥን ጋዜጠኞች በዛሬ ዕለት ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል፡፡ የኢሳት ጋዜጠኞቹን የባህልና ቱሪዝም ሚንስትሯ ዶክተር ሂሩት ካሳሁን እንዲሁም ሌሎች የመንግሥት ባለስልጣናት አቀባበል አድገውላቸዋል። በተጨማሪም የጋዜጠኞቹ ቤተሰቦች፣ አድናቂዎቻቸው እና ደጋፊዎቻቸውም ጭምር በአቀባበል ስነ ስርዓቱ ላይ ተገኝተዋል። ጋዜጠኞቹ በበኩላቸው ወደ ሃገራቸው በመግባታቸው ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው እና በሃገሪቱ […]

የኤርትራ ፐብሊክ ዲፕሎማሲና የባህል ልዑክ አዲስ አበባ ገባ

የኤርትራ የባህል እና የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን አዲስ አበባ ገባ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ አንደሚጠቁመው ከ60 በላይ አባላት ያሉትና ታዋቂው አርቲስት በረኸት መንግስተአብን ጨምሮ የተለያዩ አከላትን ያካተተ የኤርትራ የባህልና የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን አዲስ አበባ ገብቷል። ቡድኑ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማሪፊያ ሲደርስ ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር እና ከአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ […]

የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ለሀገርና ለህዝቦች ሉአላዊነት መከበር ያበረከተውን  አስተዋጽኦ አደነቁ

የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ለሀገርና ለህዝቦች ሉአላዊነት መከበር ያበረከተውን  አስተዋጽኦ አደነቁ።   መከላከያ ሰራዊቱ ለልማትና ለዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ወሳኝ የሆነው የህገ-መንግስትና የህዝቦች ሉአላዊነት ያለምንም መሸራረፍ እንዲከበር በማድረግ አርአያነት ያለው ተግባር እያከናወነ ነው ብለዋል። ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የሃገር መከላከያ ሰራዊት ቀን በዓልን ምክንያት በማድረግ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት የሀገራችንና ጎረቤት […]

የመንገድ ፈንድ ጽህፈት ቤት ባለፉት ሰባት ወራት 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን አስታወቀ

የመንገድ ፈንድ ጽህፈት ቤት ባለፉት ሰባት ወራት 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡ገቢው ለመንገድ ጥገናና ለመንገድ ደህንነት እርምጃዎች ማስፈጸሚያ ይውላል ብሏል። ጽህፈት ቤቱ ለአርትስ ቲቪ የላከው የተቋሙ የ2011 በጀት አመት የሰባት ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እንደሚያመለክተው በሰባት ወራት የስራ አፈጻጸሙ  1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ ችሏል። […]