ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በቤኒሻንጉልና ጋምቤላ ትምህርት ቤቶችን ሊያስገነቡ ነው
ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በቤኒሻንጉልና ጋምቤላ ትምህርት ቤቶችን ሊያስገነቡ ነው ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ በሁለቱ ክልሎች 20 ሚሊዮን ብር ትምህርት ቤቶቹን ለማስገንባት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ከሁለቱም ክልሎች ትምህርት ቢሮ ተወካዮች ጋር ተፈራርመዋል። እንደ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ገለፃ ለዜጎች ጥራት ያለው ትምህርት ፍትሃዊ በሆነ ሁኔታ ተደራሽማድረግ የሀገሪቱን የወደፊት ትውልድ ለማነጽ እና ለማዘጋጀት ቁልፍ ተግባር ነው ። በተያያዘ ዜናም ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የተለያዩ የውጭ ሀገር ተቋማትን በማስተባበር ያሰባሰቧቸውን የህክምና መገልገያ ቁሳቁሶች የህፃናት አልጋዎች፣የደም ማስቀመጫ ፍሪጆች እና ተሽከርካሪ የሆስፒታል ወንበሮች ለሾኔ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አስረክበዋል። የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ለአርትስ ቲቪ በላከው መግለጫ እንዳመለከተው የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት በገጠር አካባቢ በትምህርት ቤት ርቀት ምክንያት ትምህርት የሚያቋርጡ ተማሪዎችን ችግር ለመቅረፍ ባቅራቢያቸው ትምህርት ቤቶቹን እንደሚገነባ ገልጿል፡፡