loading
መጋቢት 1 ሊካሄዱ የነበሩ የ2ኛ ዙር የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች መጋቢት 8 ይካሄዳሉ ተባለ

የ2ኛ ዙር የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች መጋቢት 8 ይጀመራሉ   የ ፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ / Fasil Kenema Football Club በፌስ ቡክ ገፁ ላይ ባሰፈረው መረጃ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን  የ2ኛው ዙር የፕሪምየር ሊግ  የተስተካከለ ፕሮግራም ለክለቡ መድረሱን አስታውቋል። አስቀድሞ የወጣው መርኃ ግብር እነንደሚያሳየው የሁለተኛ ውድድር ዘመን አጋማሽ በሳምንቱ መጨረሻ እንደሚጀምር ቢያሳይም መጋቢት 1 ሊደረጉ […]

የኢትዮጵያ ሴቶች ኦሎምፒክ ቡድን መጋቢት 1 ከዩጋንዳ ጋር ይጫወታል ተባለ

የኢትዮጵያ ሴቶች ኦሎምፒክ ቡድን መጋቢት 1 ከዩጋንዳ ጋር ይጫወታል ተባለ እ.አ.አ በ2020 በጃፓን ዋና ቶክዮ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የኦሎምፒክ ውድድር፤ በሴቶች ኦሎምፒክ እግር ኳስ ውድድር የአፍሪካ ዞን የዙሩ የቅድመ ማጣሪያ ውድድር፤ ኢትዮጵያ ከ ዩጋንዳ መጋቢት 25/2011 ዓ/ም በአዲስ አበባ ስታዲየም የምትጨወት መሆኑን የአለም አቀፉ የእግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል /ፊፋ/ አስታውቆኛል ሲል የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በይፋዊ […]

በቻምፒዮንስ ሊግ አያክስ እና ቶተንሃም ወደ ሩብ ፍፃሜ አልፈዋል

በቻምፒዮንስ ሊግ አያክስ እና ቶተንሃም ወደ ሩብ ፍፃሜ አልፈዋል የ2018/19 የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የመጨረሻ 16ቱ ቡድኖች ወደ ሩብ ፍፃሜው ዙር ለመቀላቀቀል የመልስ ጨዋታቸውን እያደረጉ ነው፡፡ ትናንት ምሽት ሁለት ግጥሚያዎች ሲከናወኑ፤ አስገራሚ ውጤቶች ተመዝግብዋል፡፡ በስፔን መዲና ማድሪድ ሳንቲያጎ ቤርናቤው ላይ የኔዘርላንዱን አያክስ ያስተናገደው ሪያል ማድሪድ የ4 ለ 1 አሰቃቂ ሽንፈት ገጥሞታል፡፡ ሁለቱ ቡድኖች ከሁለት ሳምንት በፊት […]

በቻይና በሚካሄደው አለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ውድድር ኢትዮጵያውያን የፈጠራ ባለሙያዎች ተሳታፊ ይሆናሉ ተባለ

በቻይና በሚካሄደው አለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ውድድር ኢትዮጵያውያን የፈጠራ ባለሙያዎች ተሳታፊ ይሆናሉ ተባለ።   ‘ሁዋዌ’ የተሰኘው ተንቀሳቃሽ ስልክ አምራች ባዘጋጀውና ለሶስት ወራት በቆየው የቴክኖሎጂ  ውድድር  ከፍተኛ ዉጤት ያመጡ  ስድስት ተማሪዎችና አንድ መምህር እዉቅናና ሽልማት የተሰጣቸው መሆኑም ተነግሯል። ከነዚህ መካከል የላቀ ውጤት ያመጡት ይብራህ መሀሪ እና ያሬድ ረዳ የተባሉት አሸናፊ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሃገራቸውን ወክለው ቻይና በሚደረገዉ አለም […]

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኬንያ እና ሶማሊያን አስታረቁ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኬንያ እና ሶማሊያን አስታረቁ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ሸምጋይነት ኬንያ እና ሶማሊያ በመካከላቸው ያለውን ልዩነት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ተስማሙ። የኬንያው ፕሬዚዳንት አሁሩ ኬንያታና የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሙሀመድ አብዱላሂ ፋርማጆ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አደራዳሪነት  በዛሬው ዕለት በኬንያ ውይይት አድርገዋል፡፡ በዚህም በሁለቱ ሀገራት መካከል ለተፈጠረው ውጥረት መንሥኤ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ውይይት በማድረግ በመካከላቸው ያለውን […]

በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ 51 ሺህ 229 ዜጎች የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ ወጥቶላቸዋል

በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ 51 ሺህ 229 ዜጎች የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ ወጥቶላቸዋል በዕጣ ከተላለፉ ቤቶች ውስጥም 32 ሺህ 653 ቤቶች በ20/80 ፕሮግራም የተካተቱ ሲሆን ቀሪዎቹ 18 ሺህ 576 ደግሞ የ40/60 ቤቶች ናቸው። በዚህም መሰረት በዕጣ ከተላለፉ የ20/80 ፕሮግራም ቤቶች ውስጥ 1 ሺህ 248 ስቲዲዮ፣ 18 ሺህ 823 ባለ አንድ መኝታ፣ 7 ሺህ 127 ባለ […]

በኢትዮጵያ ዘላቂ የከተሞች ዕድገት ላይ ያተኮረ ዓለም አቀፍ አውደ ጥናት እየተካሄደ ነው

በኢትዮጵያ ዘላቂ የከተሞች ዕድገት ላይ ያተኮረ ዓለም አቀፍ አውደ ጥናት እየተካሄደ ነው። ጥራት ያለው የትምህርት ስርዓትን ለማስፈን አለማቀፍ ተሞክሮና ትብብር ያስፈልጋል ተብሏል። በአሜሪካ መንግስት በተዘጋጀውና በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ በሚገኘው በዚሁ አውደጥናት ላይ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ወልደማርያም እንደተናገሩት ኢትዮጵያ በመማር ማስተማር፣ በምርምርና በማህበራዊ አገልግሎት ዙሪያ ጥራት ያለው ተግባር ለማከናወን ዓለም […]

መጣል የጀመረው ዝናብ ከቀን ወደ ቀን እየተጠናከረ እንደሚቀጥል ሚትዩሮሎጂ ኤጀንሲ አስታወቀ

አዲስ አበባን ጨምሮ በሁሉም የበልግ አብቃይ አካባቢዎች መጣል የጀመረው ዝናብ ከቀን ወደ ቀን እየተጠናከረ እንደሚቀጥል የብሔራዊ ሚትዩሮሎጂ ኤጀንሲ አስታወቀ።   በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በሚቀጥለው አንድ ወር ከመደበኛ ጋር የተቀራረበ ዝናብ ይኖራቸዋል ብሏል።   በኤጄንሲው የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አህመዲን አብዱልከሪም  እንደተናገሩት በኦሮሚያ ክልል ጅማ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ የአርሲና የባሌ ከፍተኛ ቦታዎች እንዲሁም የቦረናና የጉጂ ዞኖች ከመደበኛ […]

“ሰላም እንዳይሰፍን የሚያደርጉ ግለሰቦችንና የማኅበራዊ ሚዲያ ቡድኖችን ኅብረተሰቡ ጆሮ ሊሰጣቸው አይገባም” ተባለ

ሰላም እንዳይሰፍን የሚያደርጉ ግለሰቦችንና የማኅበራዊ ሚዲያ ቡድኖችን ኅብረተሰቡ ጆሮ ሊሰጣቸው አይገባም ሲሉ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ–ጉባኤ ወይዘሮ ወርቅሰሙ ማሞ ተናገሩ።   አፈ-ጉባኤዋ ይህን የተናገሩት የአማራ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር፣ 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 12ኛ መደበኛ ጉባኤው ላይ በክልሉ የሰላም እና ደኅንነት ቢሮ የ6 ወራት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ውይይት ባደረገበት ወቅት ነው። በውይይቱ […]