loading
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 176 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸዉ 75 ሰዎች ደግሞ ማገገማቸዉ ተገለጸ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 8 ፣ 2012 በኢትዮጵያ ተጨማሪ 176 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸዉ 75 ሰዎች ደግሞ ማገገማቸዉ ተገለጸ፡፡ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ ዉ 5 ሺ 6 መቶ 36 የላብራቶሪ ምርመራ አንድመቶ ሰባስድስት ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸዉ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ አስታዉቀዋል፡፡በአጠቃላይም በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸዉ ሰዎች ቁጥር 3 ሺህ 5 መቶ 21 ደርሷል፡፡ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸዉ ሰዎች […]

ከ1ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የላብራቶሪ መሳሪያዎች ድጋፍ ተደረገ::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 8 ፣ 2012  ከ1ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የላብራቶሪ መሳሪያዎች ድጋፍ ተደረገ:: የጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀዉ ሬይ አስመጪ እና ላኪ ኃ/ተ/ግ/ድርጅት በዛሬ ዕለት ለኮሮና መከላከያ የሚውሉ የላብራቶሪ መመርመሪያ መሳሪያዎች ለ ሚኒስቴሩ አስረክበዋል ፡፡ በርክክቡም ወቅት የጤና ሚኒስቴር ተወካይ አቶ ያዕቆብ ሰማን እንደተናገሩት የተደረገው ድጋፍ ለኮሮና በሽታ ለይቶ ህክምና መስጫ ማዕከሎች አገልግሎት […]

በዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ የተከሰተው የኢቦላ ቫይረስ 11 ሰዎችን መግደሉ ተሰማ::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 9 ፣2012  በዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ የተከሰተው የኢቦላ ቫይረስ 11 ሰዎችን መግደሉ ተሰማ:: ምእራብ አፍሪካዊቷ ሪፓብሊክ ኮንጎ በአሁኑ ጊዜ ሶስት ትላልቅ ፈተናዎች ከፊቷ ተጋርጠውባታል ነው የተባለው፡፡ አንደኛው የመላው ዓለም ችግር የሆነው የኮሮና ቫይረስ፣ ሁለተኛው ደጋግሞ ያንገላታት የኢቦላ ቫይረስ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ከኩፍኝ ወረርሽኝ ጋርም እየታገለች ነው፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው በዲሞክራቲክ ኮንጎ በቅርቡ […]

የአፍሪካ ህጻናት ቀን የኢኮኖሚ ጫና ለገጠማቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ በማድረግ እየተከበረ ነው::

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2012 የአፍሪካ ህጻናት ቀን የኢኮኖሚ ጫና ለገጠማቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ በማድረግ እየተከበረ ነው:: የአፍሪካ ህጻናት ቀን በኮቪድ-19 ምክንያት የኢኮኖሚ ጫና ለገጠማቸው ዝቅተኛ የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ በማድረግና ግንዛቤ በመስጠት እየተከበረ መሆኑን የሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስቴር አስታወቀ :: ሚኒስቴሩ ለአርትስ በላከዉ መግለጫ እንዳስታወቀዉ የአፍሪካ ህጻናት ቀንን ከሰኔ 2 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ በዓሉን […]

በኒው ዚላንድ ከ24 ቀናት በኋላ ሁለት የኮሮሮናቫይረስ ታማሚዎች መገኘታቸው ተሰማ::

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2012 በኒው ዚላንድ ከ24 ቀናት በኋላ ሁለት የኮሮሮናቫይረስ ታማሚዎች መገኘታቸው ተሰማ:: ቢቢሲ በዘገባው እንዳስነበበው ኒው ዚላንድ የኮሮናቫይረስን አጥፍቻለሁ ካለች በኋላ ነው ከእንግሊዝ በመጡ ሁለት ሰዎች ቫይረሱ የተገኘው፡፡ ኒው ዚላንድ ባለፈው ሳምንት አዲስ የኮሮናቫይረስ ታማሚዎች አለመገኘታቸውን ተከትሎ በሀገር ውስጥ ጥላቸው የነበሩትን የዕንቅስቃሴ እገዳዎች ሙሉ በሙሉ አንስታለች፡፡ አሁን ላይ ከእንግሊዝ በልዩ ፈቃድ ወደ […]

የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አካል የሆነው የቤት እድሳት መርሀግብር በይፋ ተጀመረ::

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2012 የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አካል የሆነው የቤት እድሳት መርሀግብር በይፋ ተጀመረ::ኢ/ር ታከለ ኡማ በሚኖሩበት አካባቢ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ ቀነኒ ሁንዴ መኖሪያ ቤት በመገኘት የቤት እድሳት መርሀግብሩን አስጀምረዋል :: በየአካባቢው የሚገኙ ለኑሮ አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ አቅመደካማች መኖሪያ ቤታቸው የሚታደስ ይሆናል :: በመኖሪያ ቤት እድሳቱ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰጪ ወጣቶችና […]

ብራዚል ኮሮናቫይረስ ከቁጥጥሬ ውጭ አይደለም ብትልም በቀን ውስጥ የሚመዘገበው የሟችና የታማሚ ቁጥር እያሻቀበ ነው::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 10 ፣ 2012  ብራዚል ኮሮናቫይረስ ከቁጥጥሬ ውጭ አይደለም ብትልም በቀን ውስጥ የሚመዘገበው የሟችና የታማሚ ቁጥር እያሻቀበ ነው:: የፕሬዚዳት ዣየር ቦልሶናሮ የፅህፈት ቤት ሀላፊ ዋልተር ብራጋ ኔቶ በሰጡት መግለጫ በሀገራችን ኮቪድ 19 ቀውስ ፈጥሮብናል ግን ደግሞ ከቁጥጥራችን አልወጣም ማለታቸው ብዙዎቹን አስገርሟል ነው የተባለው፡፡ ምክንያቱም ሀላፊው ይህን አይነት መግለጫ የሰጡት በብራዚል በ24 በሰዓታት […]

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት መካነ-ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ በሚሆን ግምት የምግብና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 10 ፣ 2012  የኢትዮጵያ ወንጌላዊት መካነ-ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ በሚሆን ግምት የምግብና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች፡፡ ቤተክርስትያንዋ ላደረገችዉ ድጋፍ በአማራ እና አፋር ክልል በኮቪድ-19 ወረርሺኝ ሳቢያ ለችግር ለተጋለጡ 10 ሺህ ለሚሆኑ ሰዎች የሚሰራጭ ነዉ፡፡ ለደቡብ ወሎ ዞን የተደረገውን 800 ሺህ ብር በሚጠጋ ወጪ የሙቀት መለኪያ፣የምግብ ዘይት፣ዱቄትና የተለያዩ የንፅህና […]

 በፌደሬሽን ም/ቤት ፤በህግ ትርጉም ሽፋን የተላለፈዉን የፖለቲካ ዉሳኔ እንደሚቃወም ባልደራስ ለእዉነተኛ ዲሞክራሲ ገለጸ::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 10 ፣ 2012 በፌደሬሽን ም/ቤት ፤በህግ ትርጉም ሽፋን የተላለፈዉን የፖለቲካ ዉሳኔ እንደሚቃወም ባልደራስ ለእዉነተኛ ዲሞክራሲ ገለጸ::ፓርቲዉ ለአርትስ ባለከዉ መግለጫ እንዳስታወቀዉ ፤የፌደሬሽን ምክርቤት በሰኔ 3 ቀን 2012 ዓ/ም ባደረገዉ ስብሰባ ፤6ኛዉ አገራዊ እና ክልላዊ ምርጫ በዉል ላልታወቀ ዘመን እንዲራዘም እና እድሜያቸዉ መስከረም 30 ቀን 2012 ዓ/ም የሚያበቃላቸዉ ሁሉም ም/ቤቶች በስልጣናቸዉ እንዲቀጥሉ መወሰኑ አግባብንት […]

የአረንጓዴ ዐሻራ አላማ የለም አፈር መሸርሸርን ማስቀረት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ተናገሩ::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 10 ፣ 2012  የአረንጓዴ ዐሻራ አላማ የለም አፈር መሸርሸርን ማስቀረት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ተናገሩ::ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ እንዳሰፈሩት የአረንጓዴ ዐሻራ አላማ የለም አፈር መሸርሸርን ማስቀረት መሆኑን ገልጸዋል፡፡የደን ምንጣሮ እና የአየር ንብረት ለውጥ ከሌሎች መንሥኤዎች ጋር ተዳምረው በየዓመቱ በኢትዮጵያ የለም አፈር መሸርሸርን ያስከትላሉ ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ።የአረንጓዴ ዐሻራ አንዱ ግብ […]