loading
ኬንያ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባልነት ምርጫን አሸነፈች

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 12 ፣ 2012  ቢቢሲ እንደዘገበው ከአፍሪካ ሀገራት ኬንያ እና ጂቡቲ በተወዳሩበት ምርጫ ኬንያ ጂቡቲን 129 ለ62 በሆነ የድምፅ ልዩነት በማሸነፍ ነው የምክር ቤቱን መቀመጫ ያገኘችው፡፡የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጂቡቲን በብርቱ ተፎካካሪነቷ አድንቀው የአፍሪካ ህብረትን ደግሞ ለሀገራቸው ለሰጠው እውቅና አመስግነዋል፡፡ኬንያ ይህን ውድድር ማሸነፏ በአካባቢው ያላት ተሰሚነት ከፍ እያለ የመምጣቱን የሚያመላክት ነው ያሉት […]

በኢትዮጵያ የህክምና ባለሙያዎች በሚያዙት መሰረት ዴክሳሜታዞን ለኮቪድ 19 ህሙማን እንደ ድንገተኛ ህክምና ለመጠቀም ተወሰነ ።

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 12 ፣ 2012  በኢትዮጵያ የህክምና ባለሙያዎች በሚያዙት መሰረት ዴክሳሜታዞን ለኮቪድ 19 ህሙማን እንደ ድንገተኛ ህክምና ለመጠቀም ተወሰነ ።የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ እንዳስታወቁት ;ለኮቪድ-19 ህሙማን የሚውለውን ዴክሳሜታዞን የተባለውን መድሀኒት በተመለከተ በእንግሊዝ መንግስት የተካሄደውን ጥናት እና ሪፖርት በዝርዝር ተመልክተነዋል ብለዋል፡፡የህክምና ጉዳዮች አማካሪ ቡድናችን እና የጤና ባለሙያዎች አማካሪ ምክር ቤት፣ የሰጠንን ምክረ ሀሳብ […]

ባለፈው ዓመት ሕይወታቸው ያለፉ የአማራ ክልል ከፍተኛ መሪዎች የመታሰቢያ ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ ነው።

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 15 ፣ 2012  ባለፈው ዓመት ሕይወታቸው ያለፉ የአማራ ክልል ከፍተኛ መሪዎች የመታሰቢያ ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ ነው።በሥነ ሥርዓቱ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ሌሎች የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡ባለፈው ዓመት ሰኔ 15 በክልሉ በተፈጠረ የፀጥታ ችግር ሕይወታቸውን ላጡ የአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና የፀጥታ ኃይሎች መታሰቢያ መርሀ ግብር እየተካሄደ […]

ዝክረ ሰኔ 15 የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ለተሰዉ ከፍተኛ አመራሮች 1ኛ ዓመት መታሰቢያ ተከናወነ ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 15 ፣ 2012  ዝክረ ሰኔ 15 የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ለተሰዉ ከፍተኛ አመራሮች 1ኛ ዓመት መታሰቢያ ተከናወነ ፡፡በሰኔ 15 ቀን 2011ዓ.ም ለተሰዉ ከፍተኛ አመራሮች የ1ኛ አመት መታሰቢያ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ በን/ስ/ላፍቶ ክ/ከተማ ተካሂዷል። ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ እና የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ እንዲሁም […]

በጋዛ የሚገኙ አንድ ሚሊዮን ፍልስጤማዊያን ለከፋ የምግብ እጥረት ተጋልጠዋል ተባለ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2012 በጋዛ የሚገኙ አንድ ሚሊዮን ፍልስጤማዊያን ለከፋ የምግብ እጥረት ተጋልጠዋል ተባለ፡፡ እስራኤል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለፍልስጤም ስደተኞች የሚልከውን ድጋፍ እንዳይደርስ በማገዷ በጋዛ የሚኖሩ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ፍልስጤማዊያን ለምግብ እጥረት መጋለጣቸው ነው የተነገረው፡፡ አሜሪካ ለፍልስጤም ስደተኞች የሚሆን በዓመት 360 ሚሊዮን ዶላር የሚሆን እርዳታ ማቆሟ ደግሞ ጉዳቱን ያባባሰው ሌላኛው ጉዳይ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡ የምግብ […]

የቀድሞ የኢፌድሪ ኤታማጆር ሹም ጀነራል ሰዓረ መኮንን የተሰዉበት አንደኛ አመት መታሰቢያ መርሀግብር ተከናወነ።

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2012 የቀድሞ የኢፌድሪ ኤታማጆር ሹም ጀነራል ሰዓረ መኮንን የተሰዉበት አንደኛ አመት መታሰቢያ መርሀግብር ተከናወነ።በመርሀግብሩ ላይ ኢ/ር ታከለ ኡማ እና የአዲስአበባ ብልጽግና ፓርቲ ሃላፊ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ ተገኝተዋል።ጀነራል ሰዓረ ባለፈው አመት ህይወታቸው ከማለፉ ከሰዓታት በፊት ከኢ/ር ታከለ ኡማ ጋር በመሆን ከሩዋንዳ ወደ አትላስ በሚወስደው መንገድ ላይ ችግኝ በጋራ ተክለዋል።የመታሰቢያ መርሀግብሩ እየተከናወነ ያለውም […]

የአፍሪካ ህብረት በደቡብ ሱዳን ላይ ግዴታሽን አልተወጣሽም በማለት ማዕቀብ ጣለባት::

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2012 የአፍሪካ ህብረት በደቡብ ሱዳን ላይ ግዴታሽን አልተወጣሽም በማለት ማዕቀብ ጣለባት::በየኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን ልዩ መልዕክተኛ በሰጡት ማረጋገጫ ሀገሪቱ የሚጠበቅባትን መዋጮ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ መክፈል ባለመቻሏ ነው ማዕቀቡ የተጣለባት፡፡ሺንዋ የዜና ወኪል እንደዘገበው ደቡብ ሱዳን ለአፍሪካ ህብረት ያልከፈለችው ከ9 ሚሊዮን ዶላር በላይ የመዋጮ እዳ አለባት ፡፡በዚህም መሰረት ግዴታዋን ተወጥታ ህብረቱ ውሳኔውን ካላነሳላት ደቡብ […]

በህዳሴው ግድብ ውሃ አሞላል ላይ ተጽዕኖ ለመፍጠር በግብጽ በኩል የተፈፀመዉን የሳይበር ጥቃት ማክሸፉን ኤጀንሲዉ አስታወቀ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2012 በህዳሴው ግድብ ውሃ አሞላል ላይ ተጽዕኖ ለመፍጠር በግብጽ በኩል የተፈፀመዉን የሳይበር ጥቃት ማክሸፉን ኤጀንሲዉ አስታወቀ፡፡ጥቃቱ ቢፈጸም ኖሮ ፤ በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ፤ ፖሊቲካዊ እና ስነ ልቦናዊ ጉዳት ሊያስከትል ይችል እንደነበር የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ አስታዉቋል፡፡ኤጀንሲዉ ሰኔ 10፣ 12 ፣ 13 እና 14 2012 ዓ.ም መቀመጫቸዉን ግብጽ ያደረጉ የሳይበር ወንጀለኞች በኢትዮጵያ የኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ […]

በአዲስ አበባ ከተማ እየተሰሩ ያሉ ፕሮጀክቶችን በተመለከተ መረጃዎችን ማግኘትና ሀሳብ መስጠት የሚቻልበት የኪነ ህንጻ እና ከተማ ማእከል ተከፈተ።

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2012  በአዲስ አበባ ከተማ እየተሰሩ ያሉ ፕሮጀክቶችን በተመለከተ መረጃዎችን ማግኘትና ሀሳብ መስጠት የሚቻልበት የኪነ ህንጻ እና ከተማ ማእከል ተከፈተ።ማእከሉ መስቀል አደባባይ ፊትለፊት ላይ የተዘጋጀ ሲሆን የካፌ አገልግሎትና ዋይፋይ የተዘጋጀለት ነው። በማእከሉ የትኛውም ዜጋ ስለከተማዋ እቅዶችና ፕሮጀክቶች መመልከትና የራሱን ሀሳብ በፅሁፍና በድምፅ መስጠት ይችላል። የተሰጡት አስተያየቶች በቦታው የሚገኙ ባለሙያዎች በማሰባሰብ ለከንቲባው በየጊዜው […]

የዓለም ጤና ድርጅት የማህበረሰብ ጤና ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳሰበ ::

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2012 የዓለም ጤና ድርጅት የማህበረሰብ ጤና ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳሰበ ::ድርጅቱ ለዓለም መሪዎች ባስተላለፈው ጥሪ የኮሮናቫይረስን ስርጭት ለመግታትና የዜጎችን ህይዎት ለመታደግ ሁነኛው መፍትሄ የማህበሰረብ ጤናን ማጠናከር ነው ብሏል፡፡ ሀገራት የጤና ፖሊሲዎቻቸውን መፍትሄ አምጭ ማድረግና ተግባራዊነታቸውን ማረጋገጥ ተገቢ ነው ያለው የዓለም ጤና ድርጅት በተለይ በዚህ ወቅት ሁሉም የሀገራት መሪዎች ብልህነት የታከለበትአመራር መስጠት ላይ […]