loading
በትግራይ መሠረታዊ አገልግሎቶች እንዲጀመሩ የደኅንነት ማረጋገጫ መሰጠቱ ተገለጸ::

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2014 የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል የተቋረጡ መሠረታዊ አገልግሎቶችን በሚመለከት ለፌደራል መንግሥት የደኅንነት ዋስትና ደብዳቤ መላካቸው ተነግሯል፡፡ ይህ የተገለጸው የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ከአሜሪካ እና ከአውሮፓ ኅብረት ልዩ መልዕክተኞች እና ከምዕራባውያን አምባሳደሮች ጋር በመቐለ ከተገናኙ በኋላ መሆኑን ኦል አፍሪካን ዶት ኮም ዘግቧል። በዚህም መሠረታዊ አገልግሎቶቹን መልሰው ሥራ ለማስጀመር ለጥገና ወደ ትግራይ […]

ሩሲያ አሜሪካ በዩክሬኑ ጦርነት ቀጥተኛ ተሳታፊ ናት ስትል ከሰሰች፡፡

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2014 ሩሲያ አሜሪካ በዩክሬኑ ጦርነት ቀጥተኛ ተሳታፊ ናት ስትል ከሰሰች፡፡ ይህ የሞስኮ ወቀሳ የተሰማው የዩክሬን ወታደራዊ መረጃ ምክትል ሃላፊ ቫዲም ስኪቢትስኪ ከአሜሪካ የተበረከተላቸው የረዥም ርቀት የሮኬት ማስወንጨፊያ ስርዓቶች በጥሩ የሳተላይት ምስል እና እውነተኛ መረጃ አቀባይ መሆናቸውን ከገለፁ በኋላ ነው፡፡ ምክትል ሃላፊው ከቴሌግራፍ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቆይታ ከጥቃቱ በፊት በአሜሪካ እና በዩክሬን […]

የናንሲ ፔሎሲ የታይዋን ጉብኝት እውን መሆኑን ተከትሎ የቻይና ከፍተኛ እርምጃ እየተጠበቀ ነው ተባለ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2014 የናንሲ ፔሎሲ የታይዋን ጉብኝት እውን መሆኑን ተከትሎ የቻይና ከፍተኛ እርምጃ እየተጠበቀ ነው ተባለ፡፡ ያለፉት ጥቂት ቀናትን ቀልብ ስቦ የነበረው የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ የታየይዋን ጉብኝት ማክሰኞ ምሽት ይፋ መሆኑን ተከትሎ የቻይና የአስፈሪ እርምጃ ማስጠንቀቂያዎች በተከታታይ እንደሚሰሙ መገናኛ ብዙሃኑ እየዘገቡ ይገኛል፡፡፡ ቤጂንግ በአፈ-ጉባኤዋ ጉብኝት ብስጭቷን የገለፀች ሲሆን እንደ […]

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከሰጠው ብድር በተጠናቀቀው በጀት አመት 10 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን ለፀ።

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2014 የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከሰጠው ብድር በተጠናቀቀው በጀት አመት 10 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን ለፀ።ባንኩ የትግራይ ክልል ፕሮጀክቶችን ሳይጨምር የተበላሸ ብድር ደረጃውን ወደ 17 በመቶ ዝቅ ማድረግ መቻሉን አስታውቋል። የባንኩ ፕሬዝዳንት ዶክተር ዮሃንስ አያሌው በትግራይ ክልል ያሉ በርካታ ፕሮጀክቶች ወደ ተበላሸ ብድር መግባታቸው አመቱን ለባንኩ ፈታኝ አድርጎታል ብለዋል።  የገጠመውን ችግር […]

በስምንት ቀናት ውስጥ ከ127 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎችን ከአዘዋዋሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉን የጉምሩክ ኮሚሽን ገለጸ።

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2014 በስምንት ቀናት ውስጥ ከ127 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎችን ከአዘዋዋሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉን የጉምሩክ ኮሚሽን ገለጸ። ኮሚሽኑ ከሐምሌ 21 ቀን እስከ 28 2014 ዓ.ም ባደረገው ዘመቻ ነው የኮንትሮባንድ እቃዎችን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 14 ሰዎችን በቁጥጥር ስር ያዋለው፡፡ በተጠቀሱት ቀናት 118 ነጥብ 5 ሚሊዮን የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎች እና ከ9 ሚሊዮን […]

ቻይና በታይዋን ድንበር አካባቢ አዲስ ወታደራዊ ልምምድ እንደምታደርግ ይፋ አደረገች።

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2014 ቻይና በታይዋን ድንበር አካባቢ አዲስ ወታደራዊ ልምምድ እንደምታደርግ ይፋ አደረገች። የቻይና ጦር ባለፈው ሳምንት የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ ወደ ታይዋን ያደረጉትን ጉብኝት በመቃወም ያደረገውን ግዙፍ ልምምድ ለማቆም እቅድ ይዞ የነበረ ቢሆንም በማግስቱ በታይዋን አቅራቢያ በባህርና በአየር ላይ አዲስ ወታደራዊ ልምምዶችን እንደሚጀመር አስታውቋል። የቻይናው ምስራቃዊ ወታደራዊ እዝ በፀረ-ባህር ሰርጓጅ […]

የሳርቤት ጎፋ ማዞርያ የፑሽኪን ጎተራ ማሳለጫ ዘመናዊ የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ ተጠናቆ ተመረቀ።

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2014 የሳርቤት ጎፋ ማዞርያ የፑሽኪን ጎተራ ማሳለጫ ዘመናዊ የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ ተጠናቆ ተመረቀ። የመንገድ ፕሮጀክቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች በተገኙበት ተመርቆ ለአገልግሎ ክፍት ሆኗዋል፡፡ የማሳለጫ የመንገዱ በዘመናዊ መልኩ የተገነባ ሲሆን የአዲስ አበባን ስምና አለም አቀፍ ደረጃዋን በሚመጥን መልኩ የተከናወነ ስለመሆኑ ተገልጿል። የፑሽኪን አደባባይ- ጎፋ […]

በግብፅ ኮፕቲክ ቤተክርስትያን በተነሳ የእሳት አደጋ 41 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ተሰማ፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2014 በግብፅ ኮፕቲክ ቤተክርስትያን በተነሳ የእሳት አደጋ 41 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ተሰማ፡፡ በግብፅ ዋና ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን በተቀሰቀሰ የእሳት ቃጠሎ 10 ህጻናትን ጨምሮ 41 ምእመናን ህይወታቸው ማለፉን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በአደጋው ህይወት ለማዳን ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አራት ፖሊሶችን ጨምሮ 45 ሰዎች ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ጥቂቶቹ ከሆስፒታል መውጣታቸውን የሀገሪቱ ጤና […]

በጋምቤላ ክልል በአራት ወረዳዎች በደረሰ የጎርፍ አደጋ ከ4 ሺህ በላይ ሰዎች ከመኖሪያቸው መፈናቀላቸውን የክልሉ አደጋ ስጋት አመራር አገልግሎት አስታወቀ።

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2014 በጋምቤላ ክልል በአራት ወረዳዎች በደረሰ የጎርፍ አደጋ ከ4 ሺህ በላይ ሰዎች ከመኖሪያቸው መፈናቀላቸውን የክልሉ አደጋ ስጋት አመራር አገልግሎት አስታወቀ።የጎርፍ አደጋው የተከሰተው በክልሉ ደጋማው አካባቢ ሲሆን የአደጋው ተጠቂዎች በላሬ፣ መኮይ ዋንቱዋ እና ኢታንግ በተባሉ ልዩ ወረዳዎች የሚገኙ ቀበሌዎች መሆናቸው ተነግሯል፡፡ የክልሉ አደጋ ስጋት አመራር አገልግሎት ኃላፊ አቶ ጋትቤል ሙን በጎርፍ አደጋው […]

የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ለአቅመ ደካሞችና ለጎዳና ተዳዳሪዎች ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ነፃ የህክምና አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2014 የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ለአቅመ ደካሞችና ለጎዳና ተዳዳሪዎች ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ነፃ የህክምና አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡ቢሮው ለአንድ ሳምንት በሚቆየው ነፃ የምርመራ እና የህክምና አገልግሎት 17 ሺህ ያህል የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ አስታውቋል። የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል በመገኘት አገልግሎቱን ባስጀመሩበት ወቅት ህብረተሰቡ በተለያዩ […]