loading
የኮንጎው ተቃዋሚ ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪ በምርጫ ማግስት በኮቪድ-19 ምክንያት ህይዎታቸው ማለፉ ተሰማ::

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 13 ፣ 2013 የኮንጎው ተቃዋሚ ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪ በምርጫ ማግስት በኮቪድ-19 ምክንያት ህይዎታቸው ማለፉ ተሰማ:: የተቃዋሚ ፓርቲን ወክለው በእጩነት ቀርበው የነበሩት ብሪስ ፓርፋይት ለላስ በምርጫው ዋዜማ እለት ነበር በቫይረሱ መያዛቸው በመረጋገጡ ሆስፒታል የገቡት፡፡ኮለላስ ህመማቸው ሲበረታ የተሻለ ህክምና እንዲደረግላቸው ወደ ፈረንሳይ ተወስደው እንደነበርም የምርጫ ቅስቀሳ ዳይሬክተራቸው ተናግረዋል፡፡ ይሁን እንጂ እጩ ተወዳዳሪው ገና […]

ፈረንሳይ በማሊ በወሰደችው የአየር ላይ ጥቃት 19 ያልታጠቁ ንፁሃን መገደላቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ!

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 22 ፣ 2013  የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምርመራ ቡድን እንዳረጋገጠው ፣ ባለፈው ጥር ወር ፈረንሳይ በማዕከላዊ ማሊ በወሰደችው የአየር ላይ ጥቃት 19 ንፁሃንን ገድላለች፡፡ በተ.መ.ድ በማሊ ልዑክ እንዳስታወቀው ከሣተላይት በተገኙ ምስሎችና ከ 400 በላይ ሰዎችን ቃለ መጠይቅ በመስራት የተዘጋጀ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ፈረንሳይ ሪፖርቱን አስተባብላለች፡፡ በማሊ በ 2012 ሰሜናዊ ክፍል የጂሃዲስቶች ጥቃት […]

በቻድ ምርጫው እንዲደናቀፍ ቢደረግም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ እንደተሳተፈ ገዥው ፓርቲ ተናገረ ፡፡

አዲስ አበባ፣  ሚያዚያ ፡ 04፣ 2013 በቻድ ምርጫው እንዲደናቀፍ ቢደረግም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ እንደተሳተፈ ገዥው ፓርቲ ተናገረ ፡፡ በቻድ በተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ መራጮች እንዳይሳተፉ በተቃዋሚዎች ጥሪ የቀረበላቸው ቢሆንም የድምፅ አሰጣጡ በሰላማዊ መንገድ የተካሄደ መሆኑን የአፍሪካ ህብረት አስታውቋል ፡፡ እሁድ እለት የተካሄደውን የምርጫ ውጤትም ቻዳውያን እየተጠባበቁ ሲሆን የወቅቱ ፕሬዚዳንት ኢድሪስ ዴቢ ሁነኛ ተቀናቃኞች ሳይገጥሟቸው ከሰባቱ […]

የሱዳን ተለዋዋጭ አቋም

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19 ፣ 2013  ሱዳን የግድቡ ድርድር እንዲሳካ የአፍሪካ ህብረት መፍትሄ ሊያመጣ እንደሚችል ገለጸች::የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ ህብረቱ በግድቡ ዙሪያ ያሉ አለመገባባቶችን በፍጥነት ለመፍታት በሚያደርገው ጥረት እምነት አለን ብሏል፡፡ ካርቱም በግድቡ ዙሪያ ያላትን አቋም ለማስረዳት የሱዳኗ የውጭ ጉደይ ሚኒስትር ማሪያም አልማሃዲ የአፍሪካ ሀገራት ጉብኝታቸውን በይፋ ጀምረዋል፡፡ጉብኝቱ ከኬንያ ተጀምሮ ዲሞክራቲክ […]

የግብጹ አስዋን ግድብ አቅራቢያ በመሬት መንቀጥቀጥ መመታቱ ተገለጸ::

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20 ፣ 2013 የግብጹ አስዋን ግድብ አቅራቢያ በመሬት መንቀጥቀጥ መመታቱ ተገለጸ:: በግብጽ አስዋን ግድብ አቅራቢያ በትናንትናው ዕለት የመሬት መንቀጥቀጥ መመዝገቡን የአገሪቱ የአስትሮኖሚ እና ጂዮፊዚክስ ሃላፊን ጠቅሶ ኢጅፕት ኢንድፐንደንት ዘግቧል። የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ከግድቡ ደቡባዊ አቅጣጫ ላይ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ የመሬት መንቀጥቀጡም በሬክተር ስኬል መለኪያ 3 ነጥብ 1 ሆኖ መመዝገቡ ተጠቁሟል። በዚሁ መሬት […]

ኢትዮጵያ የታገሰችው የሱዳንን ህዝብ ስለምታከብር እንጂ ፈርታ አይደለም!

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26 ፣ 2013 ሱዳን ቤንሻንጉልን የራሷ ለማድረግ የምታደርገው እንቅስቃሴ እጅግ አሳፋሪ መሆኑን የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። ሱዳን የኢጋድ ሊቀመንበር ሆና እያለ በዚህ መንገድ ለመፈፀም የምትሞክረው ህገወጥ ድርጊት በኢትዮጺያ በኩል ፍፅም ተቀባይነት እንደሌለው ነው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የገለፁት፡፡ ሱዳን የኢትዮያን መሬት የመያዟና ኢትዮጵያዊያን አርሶአደረች ማፈናቀሏ ሳያንሳት ቤንሻንጉልን የራስዋ […]

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28 ፣ 2013 ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ፡፡ አቶ ደመቀ ከፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎዛ ጋር ፕሪቶሪያ ተገናኝተው ባደረጉት ውይይት በሁለቱ አገሮች የሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ፍሬያማ ውይይት ማዳረጋቸው ተመልክቷል፡፡ ምክትል ጠቅላይ መኒስትሩ በውይይታቸው ወቅት በኢትዮጵያ ያለውን ወቅታዊ ጉዳዮች በተመለከተ ለፕሬዚዳንት ራማፎዛ ገለፃ […]

ግብፅ በሁለት ሳምንታት ውስጥ 35 ዶክተሮቿን በኮሮናቫይረስ ሳቢያ ማጣቷን የሀገሪቱ የህክምና ማህበር ገለጸ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 12፣ 2013 ግብፅ በሁለት ሳምንታት ውስጥ 35 ዶክተሮቿን በኮሮናቫይረስ ሳቢያ ማጣቷን የሀገሪቱ የህክምና ማህበር ገለጸ:: ባለፈው ማክሰኞ ዶክተር ዋስፊ የተባሉ የቆዳ ስፔሻሊስት ሀኪም በሳዳር አል አባሲያ ሆስፒታል በህክምና ላይ እንዳሉ መሞታቸው የተሰማ ሲሆን በሰዓታት ልዩነት የህፃናት ሃኪም የሆኑት ዶክተር ራኒያ ፉአድ አልሰይድ ህልፈት ተሰምቷል፡፡ ሚድል ኢስት ሞኒተር የህክምና ማህበሩን ጠቅሶ እንደዘገበው […]

በቱኒዚያ የተጀመረው እስራኤልን የሚያወግዝ የተቃውሞ ሰልፍ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 12፣ 2013  በርካታ ቱኒዚያዊያን እስራኤል በጋዛ ላይ የምትፈፅመውን ጥቃት በማውገዝ የአደባባይ ሰልፍ አካሄዱ ሰልፈኞቹ በዋና ከተማዋ ቱኒዝ ሞሃመድ 5ኛ ብሎ በሚጠራው ጎዳና ተሰባስበው ከፍልስጤም ጎን መሆናቸውን በመግለጽ እስራኤልን የሚያወግዙ መፈክሮችን ሲያሰሙ ታይተዋል፡፡ በሺዎች የሚቆጠሩት ተቃዋሚ ሰልፈኞቹ በቅርቡ በቱኒዚያና በእስራኤል መካከል የተጀመረውን መደበኛ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ከወንጀል ትርታ በመመደብ እንዲሰርዝ ለሀገሪቱ ፓርላማ ጥያቄ […]

የግብፅ የአፍሪካ የክትባት ምርት ማዕከል የመሆን ዕቅድ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 16፣ 2013  ግብፅ የኮሮናቫይረስ ክትባትን በማምረት የአፍሪካ ማዕከል የመሆን ፍላጎት አለኝ አለች ካይሮ በሶስት ሳምንታት ውስጥ 2 ሚሊዮን የሲኖቫክ ክትባት ለማምረት መዘጋጀቷን የሀገሪቱ ጤና ሚኒስትር ሃላ ዛይድ ተናግረዋል፡፡ ቫሴራ በመባል የሚታወቀው የግብፅ ክትባት አምራች ኩባንያ በቻይና የሚመረተውን ሲኖቫክ የኮቪድ 19 ክትባት የማምረት ሂደት ውስጥ መግባቱንም ሚኒስትሯ ይፋ አድርገዋል፡፡ ሚኒስትሯ በሳምንቱ መጨረሻ […]