loading
አርቲስት አልማዝ ኃይሌ (ማሚ) ከዚህ አለም በሞት ተለየች።

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2013 አርቲስት አልማዝ ኃይሌ (ማሚ) ከዚህ አለም በሞት ተለየች። በበርካታ የትያትርና ፊልም ስራዎች የምትታወቀው አርቲስት አልማዝ ኃይሌ (ማሚ) ከዚህ አለም በሞት ተለየች።ለሳምንታት በህመም ላይ የነበረችው አርቲስቷ ዛሬ ማለዳ ነው ማረፏ የተሰማው።የአርቲስቷ ስርዓተ ቀብር ነገ በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይፈፀማል።

በመስቀል ደመራ በዓል የታየው የአብሮነት እና ሰላማዊ የበዓል አከባበር በኢሬቻ በዓልም ሊደገም እንደሚገባ ም/ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2013 በመስቀል ደመራ በዓል የታየው የአብሮነት እና ሰላማዊ የበዓል አከባበር በኢሬቻ በዓልም ሊደገም እንደሚገባ ም/ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡በመስቀል ደመራ በዓል የታየው የአብሮነት እና ሰላማዊ የበዓል አከባበር በኢሬቻ በዓልም ሊደገም እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታዉቀዋል። ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ የመስቀል ደመራ በዓል በሰላም በመጠናቀቁ እና የሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ […]

በዞኑ 285 የዳስ መማሪያ ክፍሎች በህንጻ ግንባታ ተለወጡ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2013 በዞኑ 285 የዳስ መማሪያ ክፍሎች በህንጻ ግንባታ ተለወጡ::በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን 285 የዳስ መማሪያ ክፍሎች ወደ ህንጻ ግንባታ መለወጣቸውን የዞኑ ትምህርት መምሪያ አስታወቀ።በሰሜን ወሎም ከ56 ሚሊዮን ብር ባላይ ወጭ የተገነቡ ትምህርተ ቤቶች ለአገልግሎት መዘጋጀታቸው ተነግሯል ። የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ትምህርት መምሪያ የግንባታ መሃንዲስ አቶ አራጋው አዲሱ ለኢዜአ […]

በፀጥታ ችግር ሳቢያ ንብረታቸውን ላጡ አሰሪዎች የድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ይፋ ሆነ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2013  በፀጥታ ችግር ሳቢያ ንብረታቸውን ላጡ አሰሪዎች የድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ይፋ ሆነ :: የድጋፍ ማሰባሰቢያው ከአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር ተያይዞ በተነሳው ሁከት ለዓመታት ሰርተው ያፈሩት ሀብትና ንብረታቸው የወደመባቸውን አሰሪዎች መልሶ ሟቋቋሚያ ነው ተብሏል።”አሰሪው ለአሰሪው” የተሰኘው ይህ መርሃ ግብር የአገሪቷን የኢኮኖሚ እድገት ለማስቀጠል፣ ማኅበራዊ መረጋጋት ለመፍጠርና ስራ ፈጣሪዎችን መልሶ ለማቋቋም […]

የወንጀል ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር የሚውሉት ድርጊታቸው ተጣርቶ መሆኑን የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አስታወቀ፡፡

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2013 የወንጀል ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር የሚውሉት ድርጊታቸው ተጣርቶ መሆኑን የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አስታወቀ፡፡በሀገሪቱ ከ2013 እስከ 2022 ለአስር ዓመታት የሚተገበረውን የተቋሙን ስትራቴጂክ እቅድ በተመለከተ ከክልል የጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ተቋማት ጋር ውይይት ተደርጓል። የፌዴራል ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አቶ ገለታ ስዩም፤ ኢትዮጵያ በ2022 ዓ.ም የአፍሪካ የፍትህ ተቋማት ተምሳሌት እንዲትሆን ለማስቻል እየተሰራ መሆኑን […]

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2013 ኮቪድ 19ን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ቁሳቁሶችን 5 ሚሊዮን ብር ወጪ በማድረግ አዮዳ አክስዮን የተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ድጋፍ አደረገ፡፡

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2013 ኮቪድ 19ን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ቁሳቁሶችን 5 ሚሊዮን ብር ወጪ በማድረግ አዮዳ አክስዮን የተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ድጋፍ አደረገ፡፡ድጋፉ የተደረገዉ ለኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሰላም ሚኒስቴር ፣ ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ፣ ለወላይታ ዞን ጤና መምሪያ ሲሆን  የኮቮድ 19 ወረርሽኝን ለመ ከላከል የሚያስችሉ የንፅህና መጠበቂያዎ ቁሳቁሶች በተለያዮ ማዕከላት ለሚገኙ ህሙማን የመተንፈሻ መሳሪያንና ማረፊያ […]

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛዉ አገር አቀፍ ምርጫን ለማካሄድ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ገለፀ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2013 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛዉ አገር አቀፍ ምርጫን ለማካሄድ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ገለፀ::ቦርዱ አያደረገ ያለዉን ዝግጅት ለጋዜጠኞች አስጎብኝቷል፡፡ምርጫ ቦርዱ ለምርጫ ከሚያስፈልጉት ቁሳቁሶች 90 በመቶ ያህሉንም ገዝቶ ማጠናቀቁን ገልጿል፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባዘጋጀዉ ጉብኝት ለምርጫ የሚያግዙትን የድምጽ አሰጣጥ ቁሳቁስና ምዝጋበ ሂደት ምን እንደሚመስል በኢግዚቢሽን ማዕከልና በኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎ ዉስጥ […]

ግብረገብነት ያለው ትውልድ ለማፍራት የስርዓተ ትምህርት ክለሳ እየተደረገ ነው::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2013 ግብረገብነት ያለው ትውልድ ለማፍራት የስርዓተ ትምህርት ክለሳ እየተደረገ ነው:: ግብረገብነት ያለው በስብዕና እውቀት የተገነባ ትውልድ ለማፍራትየስርዓተ ትምህርት ክለሳ እየተደረገ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ ::በአጠቃላይ ትምህርት እየተካሄደ ያለውን ሪፎርምና የቀጣይ አስር ዓመት መሪ እቅድ ዙሪያ የተዘጋጀ የውይይት መድረክ በአዳማ ተካሄዷየትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ በመድረኩ እንደገለጹት የአጠቃላይ ትምህርት ሴክተር የተማሪዎች […]

በሲያትል የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባላት የተለያዩ የሕክምና ቁሳቁስ ለጤና ሚኒስቴር አስረከቡ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2013 በሲያትል የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባላት የተለያዩ የሕክምና ቁሳቁስ ለጤና ሚኒስቴር አስረከቡ:: ስምንት አባላት ያሉት የልዑካን ቡድን ኮቪድ-19ን ለመከላከል የሚያስችሉ የሕክምና መሳሪያዎችና ሌሎች ቁሳቁስ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ፅዮን ተክሉና ለጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሳሕረላ አብዱላሂ አስረክበዋል::የሲያትል ኮሚኒቲ ተወካይ አቶ ፈለቀ ወልደማርያም ድጋፉ የተደረገው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን መከላከያና ሌሎች ቁሳቁስ እንደሚገኙበት ተናግረዋል በድጋፍ […]

ፕሮፌሰር መስፍንን የሚዘክር ፋውንዴሽን::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2013 የፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ሥራዎችን የሚዘክር ፋውንዴሽን ሊቋቋም መሆኑ ተገለፀ፡፡ የፕሮፌሰር መስፍን  የሥራ ባልደረባ የነበሩት አቶ ያሬድ ሃይለማርያም የሟቹን ሥራዎችን የሚዘከር ፋውንዴሽን እንደሚቋቋም ለኢዜአ ገልጸዋል። ፋውንዴሽኑን የማቋቋም ሀሳብ ከህልፈተ ህይወታቸው በፊት ሲታሰብ የነበረ ጉዳይ እንደነበረ ገልጸው፣ የፕሮፌሰር መስፍን ድንገተኛ ሞት ሐሳቡን ፈጥኖ ሥራ ላይ ለማዋል  አነሳሽ ሆኗል ብለዋል። ፋውንዴሽኑን በስድስት ወራት […]