ባለፉት 24 ዓመታት በኢትዮጵያ በትምህርትና ስልጠና ሥርዓት በታዩ ችግሮች ዙርያ ዛሬ ውይይት ይደረጋል
የኢፌዲሪ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ጥላዬ ጌቴ በጽህፈት ቤታቸው በሰጡት መግለጫ ከዛሬ ጀምሮ የሚደረገው የውይይት መድረክ ዋነኛ ዓላማ ለፍኖተ-ካርታው ዝግጅት እንዲረዳ በተዘጋጀው የመጀመሪያ ደረጃ ረቂቅ ጥናት ዙሪያ ውይይት በማድረግ ለፍኖተ-ካርታው ዝግጅት የሚረዳ ተጨማሪ ግብዓት ለማሰባሰብ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡ የማሻሻያ ሀሳቦች ዙሪያ በሚደረገው ውይይት በተሳታፊዎች የሚቀርቡ ተጨማሪ የማሻሻያ ሀሳቦች በቂ ውይይት ከተደረገባቸውና መግባባት ከተደረሰባቸው በኋላ ለ15 ዓመታት […]