መሪዎቹ ሜዳልያ ተሸለሙ
በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች አልጋወራሽ ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ነኸያን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና ለኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ሰላም እንዲሰፍን ላበረከቱት አስተዋፅኦ የሀገሪቱን ፕሬዚዳንታዊ ሜዳሊያ ሸለሙ።
በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች አልጋወራሽ ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ነኸያን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና ለኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ሰላም እንዲሰፍን ላበረከቱት አስተዋፅኦ የሀገሪቱን ፕሬዚዳንታዊ ሜዳሊያ ሸለሙ።
ባለፉት 27 ዓመት በሁለት ሲኖዶስ ስትመራ የቆየችውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ወደ አንድ ለማምጣት የሰላምና የእርቅ ጉባዔው በዋሸንግተን ደብረ ሀይል ቅዱስ ገብርዔል ቤተክርስቲያን ባለፈው እሁድ የሁለቱም ልኡካን አባቶች በተገኙበት የጋራ ጸሎትና የመክፈቻ መርሐ ግብር ተጀምሯል። በእስካሁኑ ውይይታቸው በአንድ ሲኖዶስ ለመመራት ከስምምነት ላይ መድረሳቸው ነው የተነገረው። በተጨማሪም “የሀገር ቤት ሲኖዶስ” እና “ስደተኛ ሲኖዶስ” የሚባለውን ለማስቀረት ተስማምተዋል። ይህ […]
በዚህ የሶስትዮሽ ጉባኤ ላይ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፣ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች አልጋወራሽ ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ነኸያን በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ። በሶስትዮሽ ውይይት ላይ የሶስቱ ሀገራት የኢንቨስትመንት ግንኙነት እንዲሁም ቀጠናዊ ጉዳዮች ይነሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ይህ ጥያቄ ከእርቁ በኋላ የሚመለስ ቢሆንም ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ግን ለቢቢሲ አማርኛዉ እንደተናገሩት ከሁለቱ ፓትርያሪኮች መካከል የስልጣን መንበሩ ላይ መቀመጥ ያለበት የሚለው ጥያቄ ማነቆ ሆኖ የቆየ ቢሆንም እርሱን አሁን መፍታት ብዙም አይገድም ብለዋል። ብፁዕ አቡነ ማቲያስ የአስተዳደሩን ስራ እየሰሩ፤ አቡነ መርቆሪዮስን ደግሞ በመንበራቸው ሆነው ከአስተዳደሩ ስራ ግን ገለል እንዲሉ ስማቸውም በቅዳሴ እየተጠራ በሲኖዶሱም እየተገኙ እንዲቀጥሉ […]
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በወርቅ ሜዳልያ ከተመረቁ 400 ተማሪዎች ጋር ተገናኙ፡፡ ተመራቂዎቹንም አበረታትተዋል፡፡ የወርቅ ሜዳልያ ተሸላሚ ተማሪዎቹም ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያላቸውን ክብር፣ ፍቅር እና አጋርነት ገልጸዋል፡፡
” አለም አቀፍ የቡና ቀን በምድረ ቀደምት” በሚል ቡናን ለማስተዋወቅ የመክፈቻ ፕሮግራም ተዘጋጅቷል፡፡ በአየር መንገዱ የኮርፖሬ ት ኮሙኒኬሽን ኦፊሰር አቶ አደፍርስ ታዬ ለአርትስ ቲቪ እንደተናገሩት በፕሮግራሙ የአየር መንገዱ ሰራተኞች፣የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን እና በቱሪዝም ዘርፍ የሚሰሩ ተቋማት በመገኘት የኢትጵያን ቡና በአለም ገበያ ማስተዋወቅን በተመለከተ ይመክራሉ ፡፡
ዛሬ ኢትዮ ቴሌኮምን በዋና ሥራ አስፈጻሚነት ለመምራት ኃላፊነታቸውን የተረከቡትን ወ/ት ፍሬሕይወት ታምሩን እናስተዋውቃችሁ፡፡ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኢንፎርሜሽን ሲስተም በመጀመርያ ዲግሪ ተመርቀዋል፣ እንግሊዝ ከሚገኘው ኦፕን ዩኒቨርሲቲ ደግሞ በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን የማስተርስ ዲግሪ አግኝተዋል፡፡ አዲሷ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በቴሌኮም ዘርፍ ለስምንት ዓመታት የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂውን ከመምራት አንስቶ፣ እስከ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚነት ድረስ ማገልገላቸውን ከኢትዮ ቴሌኮም ሕዝብ ግንኙነት ክፍል […]
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከ50 የተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከተዉጣጡ 3 ሺ 175 መምህራን ጋር እየተወያዩ ነው፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ እውቀት እና የአካዳሚክ ነጻነት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ለሚኖር ነጻ አስተሳሰብ ቅድመ ሁኔታዎች መሆናቸውን ተናግረዋል። ዶክተር አብይ ለመምህራኖቹ ጥያቄ በሰጡት ምላሽ በትምህርቱ ዘርፍ የተያዘውን ግብ ለማሳካትም ብቁ መምህራን እና ጥራት ያለው ትምህርት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል። ብቃት […]
ይህ የተባለዉ የካፒታል ኢንተርናሽናል ሆቴል የባህል አዳራሹን ሲያስመርቅ ነው፡፡ በካፒታል ሆቴል የባህል አደራሽ ምረቃ ስነ-ስርዓት ላይ የከተማዋ ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ እና ምክትል ከንቲባ ዳግማዊት ሞገስ የተገኙ ሲሆን ምክትል ከንቲባዋ ዳግማዊትም ከተማችን አዲስ አበባ ብዙ ባህል አዳራሾች ያስፈልጓታል ፤በባህል ላይ የሚሰሩ ባለሀብቶችንም እናበረታታለን ብለዋል፡፡ የካፒታል ሆቴል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አዲስአለም ገብሬ በሆቴላቸዉ ዉስጥ ልዩ […]
የሐገር አቀፍ ትምህርት ፈተናዎች እና ምዘና ኤጀንሲ በስሜ በሀሰት የተከፈቱ የተለያዩ የፌስ ቡክ ፔጆች የ12ኛ ክፍል ፈተና ወጥቷል፡፡ በሚል ያስወሩት ወሬ ሀሰት ነዉ ብሏል፡፡ ኤጀንሲዉ አስከ ሀምሌ 25 ግን የፈተናዉ ዉጤት ይፋ እንደሚሆን ለአርትስ ቲቪ ተናግሯል፡፡ በኤጀንሲዉ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ረዲ ሾና ለጣቢያችን ፈተናዉ ገና በእርማት ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የሀገር አቀፍ ትምህርት […]