loading
ያለምንም የፖለቲካ ልዩነት ለኢትዮጵያ ህልውና በጋራ መቆም አለብን-ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ::

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 24፣2013  ዜጎች ያለምንም የፖለቲካ ልዩነት ለኢትዮጵያ ህልውና በጋራ መቆም እንዳለባቸው የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኀበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ጥሪ አቀረቡ፡፡ የኢዜማ ፓርቲ  አመራርና አባላት “ደሜን ለእናት ሀገሬ” በሚል መሪ ሃሳብ በብሔራዊ ደምባንክ በመገኘት ደም ለግሰዋል። የፓርቲው መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የደም ልገሳ መርሃ ግብር የተዘጋጀው ፓርቲው ለሀገሩ ህልውና መስዋዕትነት እየከፈለ ላለው […]

በትግራይ ከ1 ነጥብ 4 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ውጪ ናቸው::

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 24፣2013 አሸባሪው ህወሓት በከፈተው ጦርነት ምክንያት 7 ሺህ ያህል ትምህርት ቤቶች በከፊልና ሙሉ ለሙሉ መውደማቸውን ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ። ይህ የተገለፀው ሀገር አቀፍ የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ዓመታዊ ጉባዔ እየተካሄደ ባለበት ወቅት ነው። የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ አሸባሪው ቡድን በትግራይ ከ1 ነጥብ 4 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎችንና ከ48 ሺህ በላይ መምህራንን ከትምህርት ስርዓት […]

በኢትዮጵያ ሶስተኛው ማዕበል የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በከፍተኛ ደረጃ እየተስፋፋ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 25፣2013 በኢትዮጵያ ሶስተኛው ማዕበል የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በከፍተኛ ደረጃ እየተስፋፋ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በሚኒስቴሩ የኮቪድ-19 ምላሽ አስተባባሪ አቶ መብራቱ ማሴቦ ሶስተኛው ዙር የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስርጭት ላለፉት ስምንት ሳምንታት በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ መምጣቱን ተናግረዋል። የወረርሽኙ ማዕበል በተለይ ደግሞ ከሀምሌ ወር የመጀመሪያዎቹ ሳምንታት ጀምሮ መጠነኛ መቀነስ አሳይቶ እንደነበረ መግለጻቸውን ኢትዮጰያ ፕሬስ ድርጅት ዘግቧል። ይሁን […]

በመጪው የትምህርት ዘመን ገቢራዊ የሚደረገው አዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ ይፋ ሆነ፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 25፣2013 በመጪው የትምህርት ዘመን ገቢራዊ የሚደረገው አዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ ይፋ ሆነ፡፡ ከ26 ዓመታት በፊት ጀምሮ በየአምስት ዓመቱ የስርዓተ ትምህርት ክለሳ የሚደረግ ሲሆን ለስድስተኛ ጊዜ የተዘጋጀው የአጠቃላይ ትምህርት ፍኖተ ካርታም ከ2014 ጀምሮ ለአምስት ዓመታት ይተገበራል። ነባሩ ስርዓተ ትምህርት የጥራትና አግባብነት እንዲሁም የሰው ሀብት ሰብዕና ግንባታ ጉድለቶች እንደነበሩት በጉባኤው ላይ ተነስቷል፡፡ ከቅድመ አንደኛ […]

የአፍሪካ ጊዜው አሁን ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 27፣2013 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአፍሪካ ጊዜው አሁን ነው፤ በጋራ ሆነን ከድህነት አረንቋ፣ አለመረጋጋት መውጣት እንችላለን ሲሉ ገለጹ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ አንደገለጹት በኢኮኖሚ ውህደት ሃብት እና እውቀታችንን ተጠቅመን አጀንዳ 2063ን ማሳካት እንችላለን ብለዋል፡፡ አጀንዳ 2063 በአፍሪካ ውስጥ ዘላቂ ልማት ማምጣትና የአየር ብከልትን ጨምሮ በአፍሪካ የተቀናጀ የአየር ንብረት ለውጥ […]

አራት ኢትዮጵያዊያን ሴቶች ከ100 የአፍሪካ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶች ስም ዝርዝር ዉስጥ ተካተቱ::

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 27፣2013 አራት ኢትዮጵያዊያን ሴቶች ከ100 የአፍሪካ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶች ስም ዝርዝር ዉስጥ ተካተቱ::አራት ኢትዮጵያዊያን ሴቶች ከ100 የአፍሪካ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶች ስም ዝርዝር ዉስጥ መካተታቸው ተገለፀ፡፡ በየዓመቱ 100 የአፍሪካ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶችን ስም ዝርዝር የሚያወጣው አቫንስ ሚዲያ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ 4 ኢትዮጵያዊያን በስኬታማና ተፅዕኖ ፈጣሪ 100 አፍሪካዊያን ሴቶች መዝገብ ውስጥ አካቷቸዋል። ከፕሬዚዳንቷ […]

አሸባሪው ህወሓት የእርዳታ መጋዘን በመዝረፉ ተጠያቂ ሊሆን ይገባል- የአሜሪካ ሴኔት የውጭ ጉዳይ ግንኙነት ኮሚቴ::

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 27፣2013 አሸባሪው ህወሓት የእርዳታ መጋዘን በመዝረፉ ተጠያቂ ሊሆን ይገባል- የአሜሪካ ሴኔት የውጭ ጉዳይ ግንኙነት ኮሚቴ የአሜሪካ ሴኔት የውጭ ጉዳይ ግንኙነት ኮሚቴ አባል የሆኑት ሴናተር ጂም ሪሽ የአሸባሪው ህወሓት ታጣቂዎች የእርዳታ እህል የተከማቸበትን የእህል መጋዘን በመዝረፋቸው ተጠያቂ ሊሆኑ ይገባል አሉ ፡፡ ሴናተሩ በትዊተር ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት አሸባሪው ህወሓት የዩኤስአይዲ (USAID) መጋዘንን ስለመዝረፋቸው […]

ኢትዮጵያ የአፍሪካ የነፃነት ምልክት ናት – የኡጋንዳ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 27፣2013 ኢትዮጵያ የአፍሪካ የነፃነት ምልክት ናት ሲሉ የኡጋንዳ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገለፁ አምባሳደር አለምፀሃይ መሰረት ከኡጋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጄጄ ኦዶንጎ ጋር በሁለትዮሽ፣ አካባቢያዊ እና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል። በተጨማሪም በሁለቱ ሀገራት ያለውን ዘርፈ ብዙ ግንኙነቶች ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መክረዋል። በወቅቱም የኡጋንዳ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጄጄ ኦዶንጎ፥ ኢትዮጵያ የአፍሪካ የነፃነት ምልክት […]

ደግመን ደጋግመን ለኢትዮጵያ ለመሰዋት የተዘጋጀን ነን – ሌ/ጀነራል ባጫ ደበሌ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2013 እኛ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ስለ ኢትዮጵያ መናገር ሳይሆን ህይወት የሚደገም ከሆነ ደግመን ደጋግመን ለኢትዮጵያ ለመሰዋት የተዘጋጀን ነን ሲሉ ሌ/ጀነራል ባጫ ደበሌ ተናገሩ፡፡ እኛ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ስለ ኢትዮጵያ መናገር ሳይሆን ህይወት የሚደገም ከሆነ ደግመን ደጋግመን ለኢትዮጵያ ለመሰዋት የተዘጋጀን ነን ሲሉ የአገር መከላከያ የሰራዊት ግንባታ ስራዎች ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጄነራል […]

ኢትዮጵያዊነት የተዘጉ በሮችን ማስከፈት የሚችል እውነት ነው- ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2013 የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ ኢትዮጵያዊነት የተዘጉ በሮችን ማስከፈት የሚችል እውነት ነው ሲሉ ገለጹ። ምክትል ከንቲባዋ ይህን ያሉት በዛሬው ዕለት እየተከበረ ያለውን የኢትዮጵያዊነት ቀንን ምክንያት በማድረግ በሸራተን አዲስ እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ ነው። ዛሬ እየተከበረ የሚገኘው የኢትዮጵያዊነት ቀን ከመስቀል አደባባይ ሥነ-ሥርዓት መልስ በሸራተን በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው፡፡ […]