loading
ከተለያዩ ሆስፒታሎች የተዉጣጡ የህክምና ባለሞያዎች በጅግጅጋ በተከሰተዉ ግጭት የተጎዱ ወገኖችን ለማከም ወደ ጅግጅጋ አቀኑ፡፡

ከተለያዩ ሆስፒታሎች የተዉጣጡ የህክምና ባለሞያዎች በጅግጅጋ በተከሰተዉ ግጭት የተጎዱ ወገኖችን ለማከም ወደ ጅግጅጋ አቀኑ፡፡ ሀኪሞቹ ከጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፤ከየካቲት12 እና ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኔየም ሜዲካል ኮሌጅ የተወጣጡ መሆናቸዉን የጤና ጥበቃ ምኒስትሩ ዶክተር አሚር አማን በፌስቡክ ገጻቸዉ ገልጸዋል ወደ ጂግጂጋ የተጓዙት የጤና ባለሞያዎች ሃያ አራት ናቸዉ፡፡

የሰብአዊ መብት ጥሰት ደርሶብናል ያሉ 300 የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ካህናት ፤ዲያቆናትና አገልጋዮች ፍትህ ማግኘታቸዉን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ገለጸ፡፡

ካህናቱ ከአስተዳደረዊ በደል በተጨማሪም ከስራ መባረር፤ የደሞዝ ክፍያን አለማግኘት፤ ያለቅድመ ዝግጅትና ፍትሃዊ ያልሆነ ዝውውር እንዲሁም ያለ ስራ መንገዋልል ከዋነኞቹ የመብት ጥሰቶች እንደሚካተቱ ቅሬታው የደረሰው የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ተናግሯል፡፡ በኮሚሽኑ የከፍተኛ ኮሚሽነር ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ወንድሜነህ ዘውዱ እንዳሉት ኮሚሽኑ ላለፉት ሁለት ዓመታት ጉዳዩን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጋር በመሆን ሲመረምር ቆይቶ ተገቢውን ውሳኔ አስተላልፏል ብለዋል […]

በጂግጂጋ እና ሌሎች ከተሞች የሃገር መከላከያ ሰራዊት እያደረገ ያለው የማረጋጋት ስራ መቀጠሉን የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር አቶ ሞቱማ መቃሳ ተናገሩ።

ሚኒስትሩ ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፥ የሃገር መከላከያ ሰራዊት በጂግጂጋና በሌሎች የሶማሌ ክልል ከተሞች በመግባት የማረጋጋት ስራ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። አሁን ላይ ችግሩን በአንድ ጊዜ ለመመለስ ከባድ ቢሆንም መከላከያ ሰራዊት በከተሞች በመግባት ችግር ሲፈጠር መቆጣጠርና ማረጋጋት የሚያስችል ዝግጅት ማድረጉንም ነው የተናገሩት። በስፍራው የተፈጠረውን ችግር ሙሉ በሙሉ ለማረጋጋት የአካባቢው ነዋሪዎች በተለይም የሃገር ሽማግሌዎች ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑንም ገልጸዋል። […]

በሀገር ደረጃ የሚሰራ የፎረንሲክ ማዕከል ባለመኖሩ አስቸኳይ ዉሳኔ የሚያስፈልጋቸዉን ጉዳዮች ቶሎ መርምሮ ለማወቅ እንቅፋት እየሆነ ነዉ ፡፡

በቅዱስ ጳዉሎስ ሆስፒታል የፎረንሲክ ሜዲስን ቴክኖሎጂ ሃላፊ ዶክተር እንየዉ ደባሽ ለአርትስ ቲቪ እንደተናገሩት የቅዱስ ጳዉሎስ ሆስፒታል የአስክሬን ምርመራ ፤የእድሜና የፆታ ጥቃት ሲደርስ በፎረንሲክ ክፍሉ ምርመራ ቢያደርግም፤ ከአባትነትና ከእናትነት ማረጋገጫ መሰል ዝርዝር የምረዛ ችግሮች ሲኖሩ ከሀገር ዉጪ ናሙና በመላክ ምርመራ ይደረጋል ብለዋል፡፡ በፎረንሲክ ምርመራ ባለሞያዎችን ወደ ህንድ በመላክ ለማሰልጠን ቢቻልም አገልግሎቱን በተገቢና በተቀላጠፈ መልኩ ለመስጠት መመርመሪያ […]

በኤሌክትሪክ ኃይል ታሪፍ ላይ ጭማሪ ሊደረግ ነው::

በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚዎች ላይ የታሪፍ ጭማሪ ለማድረግ አስፈላጊው ሂደት መጀመሩን የኢትዮጵያ ኢነርጂ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡ ማሻሻያው ዝቅተኛ የኃይል ተጠቃሚዎችን አያካትትም ተብሏል፡ ቢቢሲ የኢትዮጵያ ኢነርጂ ባለስልጣን ዳይሬክተር የሆኑትን አቶ ጌታሁን ሞገስን አናግሮ እንደዘገበዉ የኤሌክትሪክ ታሪፍ ጭማሪው በተለያዩ ደረጃዎች አልፎ ተቀባይነት ሲያገኝ ተግባራዊ እንደሚሆን ተናግረዋል። አቶ ጌታሁን የታሪፍ ጭማሪ ማድረግ ያስፈለገበትን ምክንያት ለመጨረሻ ጊዜ የታሪፍ ጭማሪ ተደርጎ […]

የኢንጅነር ስመኘው በቀለን ቤተሰቦችን ለመደገፍ የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ ተዋቅሯል::

በሀይደሮ ፓወር ዙሪያ የሚያጠኑና ከፍተኛ ዉጤት ለሚያገኙ ተማሪዎች ኢንጅነር ስመኘዉ በቀለ አዋርድ በሚል ለመስጠት እቅድ ተይዟል ተባለ፡፡ የኢንጅነር ስመኘው በቀለን ቤተሰቦችን ለመደገፍ የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ ተዋቅሯል:: የመንግስት ኮሙኒኬሽን በድረገጹ እንዳስታወቀዉ ሐምሌ 19 ቀን 2010 ዓ.ም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በመኪናቸው ውስጥ ህይወታቸው አልፎ የተገኙትን የኢንጅነር ስመኘው በቀለን ቤተሰቦች መደገፍ የሚያስችል የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ ተዋቅሯል። ኮሚቴው […]

በአክሱም ጽዮን ለሀገራችን ሰላም ምህላ እየተደረገ ነዉ፡፡

በምህላዉ ከ50 ሺህ ሰዉ በላይ እየታደመ እንደሚገኝ በአክሱም ጺዮን የስብከተ ወንጌል ምክትል ሀላፊ በኩረ ትጉሃን ስቡህ ለአርትስ ቲቪ ተናግረዋል፡፡ ከነሐሴ አንድ ጀምሮ የፍልሰታ ጾምን አስመልክቶ የተጀመረዉ ምህላ አስከ ጾሙ ማብቂያ ድረስ ይቀጥላል፡፡፡በአክሱም ፂዮን ሁልጊዜ ወር በገባ ከ1-7 ባሉት ቀናት ምህላ የሚደረግ ሲሆን የፍልሰታ ፆም አስመልክቶ ደግሞ እስከ ጾም ፍቺ ምህላ ይደረጋል ብለዋል፡፡ በኩረ ትጉሃን የዘንድሮዉን […]

የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦነግ) በሚቀጥሉት ሶስተ ቀናት ውስጥ ወደ ኢትዮጲያ ገብቶ ስራ ይጀምራል ተባለ::

በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው ኦነግ ወደአዲስ አበባ ልዑካን እንደሚያሰማራ እና ጽሕፈት ቤቱን ከፍቶ ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ እንደሚጀምር የድርጅቱ መሪ አቶ ዳውድ ኢብሳ ለ ቪ ኦ ኤ ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጲያ መንግስትም በአስመራ ከሚገኘው የ ኦነግ ድርጅት ጋር በኢትዮጲያ ይልቁንም በኦሮሚያ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዴት ህዝቡን ባሳተፈ መልኩፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ማድረግ እንዳለባቸው ከስምምነት መድረሳቸው ነው የተነገረው፡፡ አቶ ዳውድ ድርጅታቸው […]