loading
ሰንደቅ ጋዜጣ ተዘጋ፡፡

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ በአማርኛ ቋንቋ ታትመው ለገበያ የሚቀርቡ የግል ሳምንታዊ ጋዜጦችም “ሪፖርተር እና “አዲስ አድማስ” ብቻ ሆነዋል፡፡ ሰንደቅ ጋዜጣ የተዘጋው በየጊዜው እየናረ ከመጣው የሕትመት ዋጋ ጋር ተያይዞ ባጋጠመው ኪሳራ ምክንያት መሆኑን የሰንደቅ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ አቶ ፍሬው አበበ ለአርትስ ቲቪ ተናግረዋል፡፡ ጋዜጣው በሳውዲ አረቢያ ታስረው በሚገኙት ሼህ መሀመድ አላሙዲን ይደገፍ እንደነበር ይነገራል። ዋና አዘጋጁ ሰንደቅ […]

አንድ ሺህ አምስት መቶ የዘንድሮ ተመራቂዎች በአንድ ሰዓት ውስጥ ከቀጣሪዎች ጋር ይገናኛሉ፡፡

ይህ የሚሆነዉ በናሽናል ኬረርስ ኤክስፖ 2018 ነዉ፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ከኢትዮ ጆብስ ጋር በጋራ በመሆን ˝ ናሽናል ኬረርስ ኤክስፖ 2018 ˝ በሚል የዘንድሮ አመት ስራ ፈላጊ ተመራቄዎችን ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር የሚገናኙበት መድረክ በሚሊኒየም አዘገጅቷል፡፡ የኢትዮ ጆብስ ሪጅናል ኮርዲኔተር ወ/ሮ ህሊና ለገሰ ለአርትስ ቲቪ እንደተናገሩት ለመጀመሪያ ግዜ በተዘጋጀው አውደ ርዐዩ ቁጥራቸው አንድ ሺህ አምስት መቶ የዘንድሮ ተመራቂዎች […]

የዘንድሮው የሻደይ በዓል ከነሐሴ 16 እስከ 18 በዋግኸምራ ብሔረሰብ ዞን” ሻዴይ በዓላችን ለገጽታ ግንባታችን” በሚል መሪ ቃል በድምቀት ይከበራል፡፡

የዋግኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሰለሞን ተክሉ ለአርትስ እንደገለጹት በዓሉ በሁሉም ወረዳዎች በጎዳና ላይ ትርኢቶች እና ባህላዊ ክዋኔዎች ይከበራል ፡፡ ከበዓሉ አከባበር ጎን ለጎን በሰቆጣ ከተማ የባህል ሲምፖዚየም የሚካሄድ ሲሆን የተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፎች ይቀርባሉ ተብሏል፡፡ በዓሉን በዩኔስኮ ለማስመዝገብ እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውን ኃላፊው ተናግረዋል፡፡ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና የቀድሞው ምክትል ጠቅላይ […]

ዘንድሮ የአሸንዳ በዓል በትግራይ ክልል በድምቀት ይከበራል አለ የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ፡፡

የቢሮው ሃላፊ አቶ ዳዊት ኃይሉ ለአርትስ እንደተናገሩት በዓሉን ለማክበር አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት በመደረግ ላይ ነው ብለዋል፡፡ በዓሉ በዋነኛነት በጎዳና ላይ ትርኢቶች እና ባህላዊ ጭፈራዎች የሚደምቅ ሲሆን የፓናል ውይይት እና የፎቶ አውደርዕይ ፕሮግራሞች ጎን ለጎን እንደሚካሄዱ ኃላፊው ነግረውናል፡፡ በዓሉን ለማክበር የክልሉ ተወላጆች እንዲሁም የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገራት ጎብኚዎች ወደ ክልሉ ያቀናሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጲያ ሙስሊሞች አንድነት እና ሰላም ላይ ያተኮረ የኢለሞች አንድነት እና ትብብር ጉባኤ ተካሄደ።

የአንድነት ጉባኤው የተካሄደው በኢትዮጲያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለውጥ የጋራ ኮሚቴ አዘጋጅነት ነው፡ሀጂ ዑመር ሰኢድ የኮሚቴው ምክትል ፀሃፊ እንደገለፁት የጉባኤው አብይ አላማ የሀገራችን ሙስሊሞችን አስተባብሮ አንድነቱን ጠብቆ የሚመራ በይዘትም በአደረጃጀትም ጠንካራ እና ሁሉን አቀፍ መሪ ድርጅት የሚቋቋምበት ህግ እና አደረጃጀት የሚያመላክት ምክረ ሀሳብ ማቅረብ እንዲሁም ወደአንድነት መምጣት ነው ብለዋል፡፡ የአንድነት እና ትብብር ኮሚቴው ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ […]

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዩስን መኖሪያ ቤታቸው ድረስ በመሄድ ጎበኙዋቸው፡፡

በጉብኝቱ ላይ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካዔል ተገኝተዋል፡፡ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩም እንዳሉት አቡነ መርቆርዮስን ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በመሆን በመጎብኘታቸው ከፍ ያለ ደስታ እንደተሰማቸው ገልጸዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው ወቅት ከአቡነ መርቆርዮስ ጋር ስለይቅርባይነትና ስለፍቅር ተወያይተዋል፡፡ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ጠቅላይ ሚኒስተሩ አቡነ መርቆርዮስን መኖሪያ ቤታቸው ድረስ ተገኝተው በመጎብኘታቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ ባለፉት 26 ዓመታት […]

ዛሬ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ምክያትን በጀዋር መሃመድ የሚመራዉ ቡድን የኦሮሚያ የሚያደርገውን ጉብኝቱን ለጊዜው ማቆሙን ኦ ኤም ኤን ዘገበ።

በዛሬዉ ዕለት በሻሸመኔ ከተማ በተፈጠረ መገፋፋትና መረጋገጥ የ3 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በርከት ያሉ ሰዎች ላይ ደግሞ የአካል ጉዳት መድረሱን አቶ አዲሱ አረጋ የኦህዴድ የገጠር ፖለቲካ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አስታውቀዋል። አደጋው የደረሰው የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ዳይሬክተር አቶ ጃዋር መሃመድ እና ሌሎች የቡድኑ አባላት አቀባበል ለማድረግ በከተማዋ በተዘጋጀ ስነ ስርዓት ላይ ነዉ። በአደጋውም እስካሁን የ3 ሰዎች ህይወት […]

አቶ አህመድ ሽዴ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ኢሶህዴፓ/ ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ።

የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ኢሶዴፓ/ ማዕከላዊ ኮሚቴ ባለፉት ሶስት ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን ጥልቅ ግምገማ ማጠናቀቁን ተከትሎ ነው አቶ አህመድ ሽዴ ሊቀ መንበር አድርጎ የመረጠው። የኢሶዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ አቶ አህመድ ሽዴን በሙሉ ድምጽ በሊቀ መንበርነት መምረጡም ተገልጿል። የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ኢሶዴፓ/ ማዕከላዊ ኮሚቴ ባለፉት ሶስት ቀናት ስብሰባው በክልሉ ተፈጥሮ በነበሩው ሁኔታ […]

የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) ልኡክ ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ ገብቷል።

በግንባሩ ቃል አቀባይ አቶ አዳኒ አብዱልቃድር ሄርሞጌ የተመራው እና 3 አባላትን ያለው ልኡኩ ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሚኒስትር ደኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ አቀባበል አድርገዋል። ወደ ሀገር የገባውን ልኡክ የመሩት አቶ አዳኒ አብዱልቃድር ሄርሞጌ፥ ግንባሩ ወደ ሀገር ቤት ለመግባት የወሰነው የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ […]

መኢአድ አንቀጽ 39 እንዲሰረዝ ጠየቀ::

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) አገር ለማፍረስ የተቀመጠ ነው ያለውን የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 39 እንዲሰረዝ ጥያቄ አቀረበ፡፡ ፓርቲውን ይህን ጥያቄ በይፋ ያቀረበው ሐሙስ ነሐሴ 3 ቀን 2010 ዓ.ም. ‹‹አገር ለማፍረስ የተቀመጠው አንቀጽ 39 የወለደው ችግር የበርካታ ዜጎችን ሕይወት እየቀጠፈ ይገኛል፤›› በማለት፣ ቴዎድሮስ አደባባይ አካባቢ በሚገኘው ዋና ጽሕፈት ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት መሆኑን ሪፖርተር ዘግቧል፡፡ […]