የአፍሪካ ህብረት በዚህ ዓመት የአፍሪካ ፓስፖርትን ስራ ላይ አውላለሁ አለ
በአፍሪካ ሀገራት መካከል ነፃ እንቅስቃሴ እንዲኖር ለማድረግ ሲባል ህብረቱ በዚህ የፈረንጆች ዓመት የአፍሪካ ፓስፖርት መመሪያ ማዘጋጀትና ማተም ላይ እንደሚሰራ ይፋ አድርጓል፡፡ ፓስፖርቱን በመጭው የካቲት ወር በአዲስ አበባ በሚካሄደው 32ኛው የህብረቱ ጉባኤ እንደሚበሰር ይጠበቃል፡፡ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መህመት በአዲስ ዓመት መልዕክታቸው ‹‹ ዓባል ሀገራቱ በአህጉሪቱ የሀገራት ድንበር በቀላሉ ለመግባትና ለመንቀሳቀስ እየወሰዳችሁት ላለው እርምጃ አባል […]