loading
የታይዋን እና የቻይና  ፍጥጫ ወደ ጦርነት እንዳያመራ አስግቷል

የታይዋን እና የቻይና  ፍጥጫ ወደ ጦርነት እንዳያመራ አስግቷል የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ዥንፒንግ ሰሞኑን በተደጋጋሚ አንዲት ቻይና በሚለው ፖሊሲያቸው ታይዋንን ከእናት ሀገሯ የሚለያት የለም ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ ታይዋን በየትኛውም ጊዜ ከቻይና ወረራ ይፈፀምብኛል የሚል ስጋት እንዲገባት  በር ከፍቷል ነው ተባለው፡፡ ዋሽንግተን ፖስት እንደዘገበው የሰሞኑ የቻይና አዝማሚያ ያላማራት ታይዋን በአዲሱ ዓመት ለቤጂንግ መልዕክት በሚያስተላልፍ መልኩ […]

በቻይና ከኢቦላ ጋር የሚመሳሰል ቫይረስ መገኘቱ ተሰማ

በቻይና ከኢቦላ ጋር የሚመሳሰል ቫይረስ መገኘቱ ተሰማ በቻይና ከኢቦላ ጋር ተመሳሳይነት ያለው ቫይረስ በሌሊት ወፍ ላይ መገኘቱን ጆርናል ኔቸር ማይክሮ ባይሎጂ ላይ የተገኘ ጥናት አመለከተ። ቫይረሱ “መንገላ” የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን ከኢቦላ ጋር የሚስመሳሰል እና ሀይለኛ መሆኑን ነው ጥናቱ ያመለከተው፡፡ ቫይረሱ በቻይና ዩዋን ግዛት የሌሊት ወፍ ላይ ነው የተገኘው፡፡ ቫይረሱም በሰዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ ትኩሳት […]

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ወደ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ሴራሊዮን አቀኑ

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ወደ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ሴራሊዮን አቀኑ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሴራሊዮን ጉብኝታቸውን የሚያደርጉት ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀናት ነው። ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝቱን የሚያካሂዱት ከሴራሊዮን ፕሬዚዳንት ጁልየስ ማዳቢዩ በተደረገላቸው ግብዣ መሰረት ነው ተብሏል። በጉብኝቱ ወቅት ሁለቱ ባለስልጣናት የሴራሊዮን እና ኢትዮጵያን ወዳጅነት […]

በአለም ዙሪያ የሚገኙ የኢትዮጵያ አምባሳደሮች በሙሉ ወደአዲስ አበባ ተጠሩ

በአለም ዙሪያ የሚገኙ የኢትዮጵያ አምባሳደሮች በሙሉ ወደአዲስ አበባ ተጠሩ የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለሁሉም የኢትዮጵያ አምባሳደሮች ጥሪ ማድረጉን አስታወቀ። ከሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት እንደተገኘው መረጃ ለአምባሳደሮቹ ጥሪ የተደረገው በተለያዩ ወቅታዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮች ላይ ገለፃ ለማድረግ ተብሎ ነው። አምባሳደሮቹ ወደአዲስ አበባ የሚመጡት በቀጣዩ ሳምንት ነው ተብሏል።

ቻይና እኛም ቤት ሚሳኤል አለ የሚል መልእክት ለአሜሪካ አስተላልፋለች

  ቻይና እኛም ቤት ሚሳኤል አለ የሚል መልእክት ለአሜሪካ አስተላልፋለች አሜሪካ የቅኝት ነፃነት በሚል ሰበብ በደቡባዊ ቻይና ባህር የምታደርገው የቅኝት እንቅስቃሴ ያሰጋት ቤጂንግ ባለስቲክ ሚሳኤሎችን ለማሰማራት መወሰኗን ይፋ  አድርጋለች፡፡ ሲ ኤን ኤን እንደዘገበው ቻይና አሰማራቸዋለሁ ያለቻቸው ዲ ኤፍ 26 የተባሉት ሚሳኤሎች እስከ 5 ሺህ 471 ኪሎ ሜትሮችን አቆራርጠው ተፈላጊው ኢላማ መምታት የሚችሉ ናቸው፡፡ የቻይናው የውጭ […]

ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ 147 ጠበቆች ላይ የዲሲፕሊን እርምጃ ወሰደ 

ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ 147 ጠበቆች ላይ የዲሲፕሊን እርምጃ ወሰደ  በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የጠበቆች አስተዳደር እና የነፃ የህግ ድጋፍ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፍቃዱ ደምሴ እንደገለጹት  በ2011ዓ.ም ስድስት ወራት ውስጥ 147 ጠበቆች የስነስርዓት እርምጃ ተወስዶባቸዋል። እንደ ጠቅላይ አቃቢ ህግ ገለፃ የተቀጡት ጠበቆች በስነ ምግባር ችግር ፣ፈቃድ በወቅቱ ባለማሳደስ እና በስነ ምግባር ችግር ጥፋተኛ የተባሉ ናቸው።  

ፖምፒዮ የኢራንን ተፅዕኖ መቀነስ የሚያስችል ተልእኮ ይዘው መካከለኛው ምስራቅን እየጎበኙ ነው

ፖምፒዮ የኢራንን ተፅዕኖ መቀነስ የሚያስችል ተልእኮ ይዘው መካከለኛው ምስራቅን እየጎበኙ ነው፡፡   የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ ኢራን በመካለኛው ምስራቅ መረጋጋት እንዳይኖር ለፈፀመችው ተግባር ተጠያቂ ያደረጉት የቀድሞውን ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባን ነው፡፡ ምክንያታቸው ደግሞ ኦባማ በቀጠናው ላለው አለመረጋጋት የኢራንን ሚና ቀላል  አድርገው መመልከታቸው ነው፡፡ ጉብኝታቸውን በዮርዳኖስ የጀመሩት ፖምፒዮ  በቀጣዩ ጉዟቸው ወደ ግብፅ ነው ያቀኑት፡፡   ካይሮ […]

የኖቤል ተሸላሚው ሳይንቲስት በዘረኛ ንግግራቸው ማዕረጋቸውን ተቀሙ

የኖቤል ተሸላሚው ሳይንቲስት በዘረኛ ንግግራቸው ማዕረጋቸውን ተቀሙ አሜሪካዊው ሳይንቲስት ዶክተር ጄምስ ዋትሰን በአንድ የቴሌቭዥን ፕሮግራም ላይ ዘረኛ ንግግር ካደረጉ በኋላ  ማዕረጋቸውን ተነጥቀዋል። በዘረ መል ምህንድስና ምርምር የሚታወቁት የኖቤል ተሸላሚው ሳይንቲስት የጥቁሮችና የነጮች ዐዕምሮ ምጥቀት በዘረ መላቸው ይወሰናል የሚል ዘረኛ ንግግር አድርገዋል። ሳይንቲስቱ እንደ አውሮፓውያኑ  አቆጣጠር በ2007 ተመሳሳይ ዘረኛ አስተያየት ሰንዝረው ይቅርታ ጠይቀው ነበር።