የሚኒስትሮች ም/ቤት ባካሄደው 61ኛ መደበኛ ስብሰባ በሁለት ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል ።
የሚኒስትሮች ም/ቤት ጥር 4 ቀን 2011 ባካሄደው 61ኛ መደበኛ ስብሰባ በሁለት ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ የሚከተሉትን ውሳኔ አሳልፏል። ሙሉውን እነሆ
የሚኒስትሮች ም/ቤት ጥር 4 ቀን 2011 ባካሄደው 61ኛ መደበኛ ስብሰባ በሁለት ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ የሚከተሉትን ውሳኔ አሳልፏል። ሙሉውን እነሆ
የገቢዎች ሚኒስቴር በታህሳስ ወር ከሀገር ውስጥ ታክስ 8.5 ቢሊየን ብር ሰበሰብኩ አለ። የገቢዎች ሚኒስቴር በታህሳስ ወር ከሀገር ውስጥ ታክስ ለመሰብሰበሰ ካቀደው 10ነጥብ 2 ቢሊየን ብር 8 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር የሰበሰበ ሲሆን ፤አፈፃፀሙም 83ነጥብ 5 በመቶ መሆኑን የሚኒስቴር መ/ቤቱ የሀገር ውስጥ ታክስ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ መሀመድ አብዱ ገልፀዋል፡፡ እንደ አቶ መሀመድ ገለፃ ለዕቅዱ አለመሳካት […]
ግንባታዎችን የሚያጓትቱ ኮንትራክተሮች እና አማካሪዎችን የከተማ አስተዳደሩ አስጠነቀቀ። “በተለያየ ምክንያት ግንባታዎችን የሚያጓትቱ ኮንትራክተሮች እና አማካሪዎችን የከተማ አስተዳደሩ ከዚህ በኃላ አይታገስም አሉ ኢ/ር ታከለ ኡማ። ኢ/ር ታከለ ኡማ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚያከናውናቸው ፕሮጀክቶች ላይ ለሚሳተፉ የህንፃ ተቋራጭ ባለቤቶች እና አማካሪዎች የስራ መመርያ ሰጥተዋል፡፡ በመድረኩ ላይ የኮንስትራክሽን ዘርፉ ለብክነት የተጋለጠ እንደነበርም አንስተዋል፡፡ በግንባታ ላይ ያሉ ነባር […]
የሳምንቱ ተጠባቂ ግጥሚያ በቶተንሃም ሆትስፐር እና ማንችስተር ዩናይትድ መካከል ምሽት 1፡30 ይከናወናል፡፡
ጅማ አባ ጅፋር በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ተሸንፏል የ2018/19 የቶታል ካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ወደ ምድብ ድልድል ለመቀላቀል የደርሶ መልስ የመጀመሪያ ጨዋታዎች ተካሂደዋል፡፡ ትናንት የሞሮኮውን ሃሳኒያ ዩኒዬን ስፖርት አጋዲር በአዲስ አበባ ስታዲየም ያስተናገደው ጅማ አባ ጅፋር የ 1 ለ 0 ሽንፈት አስተናግዷል፡፡ ሙሉ ጨዋታው በጣት ከሚቆጠሩ የግብ ሙከራዎች ውጭ ያን ያህል ሳቢ ያልነበረ፤ በሁለቱ ቡድኖች ያን ያህልም ኢላማውን […]
ማንችስተር ዩናይትድንና ሶልሻዬርን የሚያቆማቸው ጠፍቷል ቀያይ ሰይጣኖቹ ሞሪንሆን አሰናብተው የቀድሞ ተጫዋቻቸውን ኦሌ ጉናር ሶልሻዬር በአሰልጣኝነት ከቀጠሩ በኋላ በተከታታይ በድል መንገድ ላይ ቢገኙም ጉዟቸው በቶተንሃም ትናንት ሊገታ እንደሚችል ተገልፆ ነበር፡፡ ይሁን እንጅ በግዙፉ ዊምብሌ ስታዲዬም ያደረገውን የፕሪምየር ሊግ 22ኛ መርሀግብር ግጥሚያ ተፈትኖም ቢሆን በጠባብ የግብ ልዩነት አሸንፎ ወጥቷል፡፡ ጨዋታውን ማንችስተር 1 ለ 0 ሲረታ የድል ጎሏን […]
በመዲናዋ አዳዲስ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ተጧጡፈዋል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 1.4 ኪሎ ሜትር ርዝመትና 30 ሜትር ስፋት ያለውን የሽሮሜዳ ቁስቋም አስፓልት መንገድ እንዲሁም ከ5 ኪሎ ሜትር በላይ ርዝመትና 25 ሜትር ስፋት ያለው የአቃቂ ቱሉ ዲምቱ የአስፓልት መንገድ ፕሮጀክቶችን አስጀምሯል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪና የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊው ዶክተር ሰለሞን ኪዳኔ […]
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከፋይናንስ ተቋማት ኃላፊዎችና ተወካዮች ጋር ተወያዩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተቋማቱ ሀላፊዎች እና ተወካዮች ጋር በዘርፉ ማሻሻያዎች ዙሪያ ነው የተወያዩት ፡፡ ውይይቱ የተደረገው ዘርፉ ብቁ ተፎካካሪ እንዲሆን እና ኢኮኖሚን ለማሳደግ ያለውን ሚና ለማጠናከር ነው ተብሏል፡፡ ውይይቱ እስካሁን በፋይናሱ ዘርፍ በተደረጉት ለውጦች፣ የፖሊሲ እና የአስተዳደር ችግሮችን መለየት እና ኃላፊነቶች ግልፅ ማድረግ ላይ ያተኮረ እንደነበርም […]
ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ በአሁኑ ሰዓት ከዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲፕሎማቶች ጋር በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ዙሪያ ውይይት እያደረጉ ነው። ጠ/ሚሩ እንደ ዲፕሎማት ዓለም አቀፋዊ አዝማሚያዎችን በመረዳት በኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ላይ የተመሰረተ ሀሳብና አሠራር መመስረት አስፈላጊ መሆኑን አፅንዖት ሰጥተዋል። በተጨማሪም ዲፕሎማቶች የመንግስት ፖሊሲን የመተግበር፤ የሚመደቡባቸውን አገራት ፖሊሲ የመገንዘብና በአገራቱ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መብት የማስጠበቅ ሚና እንዳላቸው አስታውሰዋል። […]